bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Psalms 23
Psalms 23
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
1
ምድር በሞላዋ የእግዚአብሔር ናት፥ ዓለምም በእርስዋም የሚኖሩ ሁሉ።
2
እርሱ በባሕሮች መሥርቶአታልና፥ በፈሳሾችም አጽንቶአታልና።
3
ወደ እግዚአብሔር ተራራ ማን ይወጣል? በተቀደሰ ስፍራውስ ማን ይቆማል?
4
ልቡ ንጹሕ የሆነ፥ እጆቹም የነጹ፥ በነፍሱ ላይ ከንቱን ያልወሰደ፥ ለባልንጀራውም በሽንገላ ያልማለ።
5
እርሱ ከእግዚአብሔር ዘንድ በረከትን ይቀበላል፥ ምሕረቱም ከአምላኩ ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው።
6
ይህች ትውልድ እርሱን ትፈልገዋለች፥ የያዕቆብን አምላክ ፊት ትፈልጋለች።
7
እናንተ መኳንንት! በሮችን ክፈቱ፥ የዘለዓለም ደጆችም ይከፈቱ፥ የክብርም ንጉሥ ይግባ።
8
ይህ የክብር ንጉሥ ማን ነው? ብርቱና ኀያል እግዚአብሔር ነው፥ እግዚአብሔር በጦርነት ኀያል ነው።
9
እናንት መኳንንት፥ በሮችን ክፈቱ፥ የዘለዓለም ደጆችም ይከፈቱ፥ የክብርም ንጉሥ ይግባ።
10
ይህ የክብር ንጉሥ ማን ነው? የኀያላን አምላክ እግዚአብሔር፥ እርሱ የክብር ንጉሥ ነው።
← Chapter 22
Chapter 24 →