bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Psalms 148
Psalms 148
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
1
እግዚአብሔርን ከሰማያት አመስግኑት፤ በአርያም ያመሰግኑታል፤
2
መላእክቱ ሁሉ ያመሰግኑታል፤ ሠራዊቱ ሁሉ ያመሰግኑታል።
3
ፀሐይና ጨረቃ ያመሰግኑታል፤ ከዋክብትና ብርሃን ሁሉ ያመሰግኑታል።
4
ሰማየ ሰማያት፥ ከሰማያት በላይ ያለ ውኃም ያመሰግኑታል።
5
የእግዚአብሔርንም ስም ያመሰግናሉ። እርሱ ብሎአልና፥ ሆኑ፤ እርሱ አዝዞአልና፥ ተፈጠሩ፤
6
ለዘለዓለም አቆማቸው፤ ትእዛዝን ሰጣቸው፥ አላለፉምም።
7
እባቦችና ጥልቆች ሁሉ፥ እግዚአብሔርን ከምድር አመስግኑት፤
8
እሳትና በረዶ፥ አመዳይና ውርጭ፥ ቃሉን የሚያደርግ ዐውሎ ነፋስም፤
9
ተራሮችና ኮረብቶችም ሁሉ፥ የሚያፈራም ዛፍ ዝግባም ሁሉ፤
10
አራዊትም፥ እንስሳትም ሁሉ፥ ተንቀሳቃሾችም፥ የሚበርሩ ወፎችም፤
11
የምድር ነገሥታት፥ አሕዛብም ሁሉ፥ አለቆች፥ የምድርም ፈራጆች ሁሉ፤
12
ጐልማሶችና ደናግል፥ ሽማግሌዎችና ልጆች፤
13
የእግዚአብሔርን ስም ያመሰግናሉ። ስሙ ብቻውን ከፍ ከፍ ብሎአልና፥ በሰማይና በምድር ያመሰግኑታል።
14
የሕዝቡንም ቀንድ ከፍ ከፍ ያደርጋል፤ የጻድቃኑንም ሁሉ ምስጋና ወደ እርሱ ለቀረበ ለእስራኤል ልጆች ሕዝብ ከፍ ከፍ ያደርጋል።
← Chapter 147
Chapter 149 →