bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Psalms 149
Psalms 149
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
1
እግዚአብሔርን አዲስ ምስጋናን አመስግኑት፤ ምስጋናውም በጻድቃኑ ጉባኤ ነው።
2
እስራኤል በፈጣሪው ደስ ይለዋል፥ የጽዮንም ልጆች በንጉሣቸው ሐሤትን ያደርጋሉ።
3
ስሙን በደስታ ያመሰግናሉ፥ በከበሮና በበገና ይዘምሩለታል።
4
እግዚአብሔር በሕዝቡ ደስ ብሎታልና፥ የዋሃንንም በማዳኑ ከፍ ከፍ ያደርጋልና።
5
ጻድቃን በክብሩ ይመካሉ፤ በመኝታቸውም ላይ ሐሤትን ያደርጋሉ።
6
እግዚአብሔርን በጕሮሮአቸው ያመሰግኑታል፤ ሁለት አፍ ያለውም ሰይፍ በእጁ ነው፥
7
በአሕዛብ ላይ በቀልን ያደርግ ዘንድ፥ ሕዝቡንም ይዘልፋቸው ዘንድ፤
8
ንጉሦቻቸውንም በእግር ብረት፥ አለቆቻቸውንም በሰንሰለት ያስራቸው ዘንድ፤
9
የተጻፈውን ፍርድ በእነርሱ ላይ ያደርግ ዘንድ። ይህች ክብር ለጻድቃኑ ሁሉ ናት።
← Chapter 148
Chapter 150 →