bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Psalms 147
Psalms 147
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
1
ኢየሩሳሌም ሆይ፥ እግዚአብሔርን አመስግኚ፥
2
ጽዮንም ሆይ፥ አምላክሽን አመስግኚ፤ የደጆችሽን መወርወሪያ አጽንቶአልና፥ ልጆችሽንም በውስጥሽ ባርኮአልና።
3
ለወሰኖችሽም ሰላምን አደረገ፥ የስንዴንም ስብ አጠገበሽ።
4
ቃሉን ወደ ምድር ይልካል፥ ነገሩም እጅግ ፈጥኖ ይሮጣል።
5
በረዶውን እንደ ባዘቶ ይሰጣል፤ ጉሙን እንደ አመድ ይበትነዋል፤
6
በረዶውን እንደ ፍርፋሪ ያወርዳል፤ ቅዝቃዜውንስ ማን ይቋቋማል?
7
ቃሉን ልኮ ያቀልጠዋል፤ ነፋሱን ያነፍሳል፥ ውኆችንም ያፈስሳል።
8
ቃሉን ለያዕቆብ፥ ሥርዐቱንና ፍርዱንም ለእስራኤል ይናገራል።
9
ለሌሎች አሕዛብ ሁሉ እንዲህ አላደረገም፥ ፍርዱንም አልገለጠላቸውም።
← Chapter 146
Chapter 148 →