bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Psalms 146
Psalms 146
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
1
እግዚአብሔርን አመስግኑ፥ መዝሙር መልካም ነውና። ለአምላካችንም ምስጋና ማቅረብ ያማረ ነው።
2
እግዚአብሔር ኢየሩሳሌምን ይሠራታል፥ ከእስራኤልም የተበተኑትን ይሰበስባል።
3
ልባቸው የቈሰለውን ይፈውሳል፥ ቍስላቸውንም ያደርቅላቸዋል።
4
ከዋክብትንም በሙሉ ይቈጥራቸዋል፥ ሁሉንም በየስማቸው ይጠራቸዋል።
5
እግዚአብሔር ታላቅ ነው፥ ኀይሉም ታላቅ ነው፥ ለጥበቡም ቍጥር የለውም።
6
እግዚአብሔር የዋሃንን ያነሣቸዋል፥ ኃጥአንን ግን እስከ ምድር ድረስ ያዋርዳቸዋል።
7
ለእግዚአብሔር በምስጋና ዘምሩ፥ ለአምላካችንም በመሰንቆ ዘምሩ፤
8
ሰማዩን በደመናት የሚሸፍን፥ ለምድርም ዝናምን የሚያዘጋጅ፥ ሣርን በተራሮች ላይ፥ ልምላሜውንም ለሰው ልጆች አገልግሎት የሚያበቅል፥
9
ለእንስሶችና ለሚጠሩት ለቍራዎች ጫጩቶች፥ ምግባቸውን የሚሰጣቸው እርሱ ነው።
10
የፈረስን ኀይል አይወድድም፥ በሰውም ጕልበት ደስ አይለውም።
11
እግዚአብሔር በሚፈሩት፥ በምሕረቱም በሚታመኑ ደስ ይለዋል።
← Chapter 145
Chapter 147 →