bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Psalms 141
Psalms 141
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
1
በቃሌ ወደ እግዚአብሔር ጮኽሁ፤ በቃሌ ወደ እግዚአብሔር ለመንሁ።
2
ልመናዬን በፊቱ አፈስሳለሁ፤ መከራዬንም በፊቱ እናገራለሁ።
3
ሰውነቴ በላዬ ላይ ባለቀች ጊዜ አቤቱ፥ መንገዴን አንተ ታውቃለህ፤ በምሄድባት በዚያች መንገድ ወጥመድን ሰወሩብኝ።
4
ወደ ቀኝም ተመልሼ አየሁ፥ የሚያውቀኝም አጣሁ፤ መሸሸጊያም የለኝም፥ ስለ ሰውነቴም የሚመራመር የለም።
5
አቤቱ፥ ወደ አንተ ጮኽሁ፦ “አንተ ተስፋዬ ነህ፥ በሕያዋንም ምድር አንተ ዕድል ፋንታዬ ነህ” አልሁ።
6
እጅግ ተዋርጃለሁና ወደ ልመናዬ ተመልከት፤ በርትተውብኛልና ከከበቡኝ አድነኝ።
7
አቤቱ፥ ስምህን አመሰግን ዘንድ ሰውነቴን ከእሥራት አውጣት፤ ዋጋዬን እስክትሰጠኝ ድረስ ጻድቃን እኔን ይጠብቃሉ።
← Chapter 140
Chapter 142 →