bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Psalms 142
Psalms 142
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
1
አቤቱ፥ ጸሎቴን ስማ፥ በእውነትህ ልመናዬን አድምጥ፥ በጽድቅህም መልስልኝ።
2
ሕያው ሁሉ በፊትህ አይጸድቅምና ከባሪያህ ጋር ወደ ክርክር አትግባ።
3
ጠላት ነፍሴን ከብቦአታልና ሕይወቴንም በምድር ውስጥ አዋርዶአታል፥ ቀድሞ እንደ ሞተ ሰው በጨለማ አኖሩኝ።
4
ሰውነቴ በላዬ አለቀችብኝ፥ ልቤም በውስጤ ደነገጠብኝ።
5
የቀድሞውን ዘመን ዐሰብሁ፥ ሥራህንም ሁሉ አነበብሁ፤ የእጅህንም ሥራ አነብባለሁ።
6
እጆቼን ወደ አንተ ዘረጋሁ፤ ነፍሴም እንደ ምድረ በዳ አንተን ተጠማች።
7
አቤቱ፥ ፈጥነህ ስማኝ፥ ሰውነቴ አልቃለች፤ ፊትህንም ከእኔ አትመልስ፥ ወደ ጕድጓድም እንደሚወርዱ አልሁን።
8
አቤቱ፥ አንተን ታምኛለሁና፥ በማለዳ ምሕረትህን አሰማኝ፤ አቤቱ፥ ነፍሴን ወደ አንተ አንሥቻለሁና የምሄድባትን መንገድ ምራኝ።
9
አቤቱ፥ ወደ አንተ ተማጽኛለሁና ከጠላቶቼ አድነኝ።
10
አቤቱ፥ አንተ አምላኬ ነህና ፈቃድህን ለማድረግ አስተምረኝ፤ ቅዱስ መንፈስህም በጽድቅ ምድር ይምራኝ።
11
አቤቱ፥ ስለ ስምህ ሕያው አድርገኝ፤ ስለ ጽድቅህም ነፍሴን ከመከራዋ አውጣት።
12
በፈቃድህ ጠላቶቼን አጥፋቸው፥ እኔ ባሪያህ ነኝና ነፍሴን የሚያስጨንቁአትን ሁሉ አጥፋቸው።
← Chapter 141
Chapter 143 →