bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Psalms 137
Psalms 137
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
1
አቤቱ፥ በፍጹም ልቤ አመሰግንሃለሁ፥ የአፌን ነገር ሁሉ ሰምተኸኛልና፤ በመላእክት ፊት እዘምርልሃለሁ።
2
በቤተ መቅደስህም እሰግዳለሁ፤ ስለ ምሕረትህና ስለ እውነትህም ስምህን አመሰግናለሁ፥ በሁሉ ላይ ቅዱስ ስምህን ከፍ ከፍ አድርገሃልና።
3
በጠራሁህ ቀን በፍጥነት አድምጠኝ፤ ነፍሴን በኀይልህ በብዙ አጸናሃት።
4
አቤቱ፥ የምድር ነገሥታት ሁሉ ያመሰግኑሃል፤ የአፍህን ቃል ሁሉ ሰምተዋልና።
5
በእግዚአብሔርም ምስጋና ይዘምራሉ። የእግዚአብሔር ክብር ታላቅ ነውና።
6
እግዚአብሔር ከፍ ያለ ነውና፥ የተዋረዱትንም ይመለከታልና፤ ትቢተኛውንም ከሩቁ ያውቀዋል።
7
በመከራ መካከል እንኳ ብሄድ፥ አንተ ታድነኛለህ፤ በጠላቶች ቍጣ ላይ እጆችህን ትዘረጋለህ፥ ቀኝህም ያድነኛል
8
እግዚአብሔርም ይበቀልልኛል፤ አቤቱ፥ ምሕረትህ ለዘለዓለም ነው፤ አቤቱ የእጅህን ሥራ ቸል አትበል።
← Chapter 136
Chapter 138 →