bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Psalms 136
Psalms 136
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
1
በባቢሎን ወንዞች አጠገብ በዚያ ተቀመጥን፤ ጽዮንንም ባሰብናት ጊዜ አለቀስን።
2
በአኻያ ዛፎችዋ ላይ በገናዎቻችንን ሰቀልን።
3
የማረኩን በዚያ የዝማሬ ቃል ጠይቀውናልና፥ የወሰዱንም፥ “የጽዮንን ዝማሬ ዘምሩልን” አሉን።
4
የእግዚአብሔርን ዝማሬ በባዕድ ምድር እንዴት እንዘምራለን?
5
ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ብረሳሽ፥ ቀኜ ትርሳኝ።
6
ባላስብሽ፥ ምላሴ በጕሮሮዬ ይጣበቅ፤ ከደስታዬ ሁሉ በላይ ኢየሩሳሌምን ባልወድድ።
7
አቤቱ፥ በኢየሩሳሌም ቀን፦ “እስከ መሠረቷ ድረስ አፍርሱ አፍርሱ” ያሉአትን የኤዶምን ልጆች ዐስብ።
8
አንቺ ወራዳ የባቢሎን ልጅ ሆይ፥ ስለ ተበቀልሽን የሚበቀልሽ ብፁዕ ነው።
9
ሕፃናቶችሽን ይዞ በዓለት ላይ የሚፈጠፍጣቸው ብፁዕ ነው።
← Chapter 135
Chapter 137 →