bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Psalms 138
Psalms 138
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
1
አቤቱ፥ ፈተንኸኝ፥ ዐወቅኸኝም።
2
አንተ መቀመጤንና መነሣቴን ታውቃለህ። የልቤን ዐሳብ ሁሉ ከሩቁ ታስተውላለህ።
3
ፍለጋዬንና መንገዴን አንተ ትመረምራለህ፤ መንገዶቼን ሁሉ አስቀድመህ ዐወቅህ፥
4
የዐመፃ ቃል በአንደበቴ እንደሌለ።
5
አቤቱ፥ አንተ እነሆ፥ የቀድሞውንና የኋላውን ሁሉ ዐወቅህ፤ አንተ ፈጠርኸኝ፥ እጅህንም በላዬ አደረግህ።
6
ዕውቀትህ በእኔ ላይ ተደነቀች፤ በረታችብኝ፥ ወደ እርሷም ለመድረስ አልችልም።
7
ከመንፈስህ ወዴት እሄዳለሁ? ከፊትህስ ወዴት እሸሻለሁ?
8
ወደ ሰማይ ብወጣ፥ አንተ በዚያ አለህ፤ ወደ ጥልቁም ብወርድ፥ አንተ በዚያ አለህ፤
9
እንደ ንስርም ክንፍን ብወስድ፥ እስከ ባሕር መጨረሻም ብበርር፥
10
በዚያ እጅህ ትመራኛለች፥ ቀኝህም ታኖረኛለች።
11
በእውነት ጨለማ ይሸፍነኛል ብል፥ ሌሊት በደስታዬ ብርሃን ይሆናል፤
12
ጨለማ በአንተ ዘንድ አይጨልምምና፥ ሌሊትም እንደ ቀን ታበራለችና፤ እንደ ጨለማዋ እንዲሁ ብርሃንዋ ነው።
13
አቤቱ፥ አንተ ኵላሊቴን ፈጥረሃልና፥ ከእናቴ ማኅፀን ጀምሮ ተቀበልኸኝ።
14
በመፈራት የተደነቅህ ነህና አቤቱ፥ አመሰግንሃለሁ፤ ሥራህ ድንቅ ነው፥ ነፍሴም እጅግ ትረዳዋለች።
15
በስውር የሠራኸው አጥንቴ ከአንተ አልተሰወረም፥ አካሌም ከምድር በታች፥
16
ያልተሠራ አካሌንም ዐይኖችህ አዩ፤ ሁሉም በመጽሐፍህ ተጻፉ፥ በቀን ይፈጠራሉ፥ ነገር ግን ከእነርሱ አንድ ስንኳ አይኖርም።
17
አቤቱ፥ ወዳጆችህ በእኔ ዘንድ እጅግ የከበሩ ናቸው፤ ከቀደምቶቻቸውም እጅግ ጸኑ።
18
እቈጥራቸዋለሁ፥ ከአሸዋም ይልቅ ይበዛሉ፤ ተነሣሁ፥ ገናም ከአንተ ጋር ነኝ።
19
አቤቱ፥ አንተ ኃጥኣንን የምትገድል ከሆንህስ፥ የደም ሰዎች ሆይ፥ ከእኔ ፈቀቅ በሉ።
20
በዐሳባቸው ይኰራሉና፤ ከተሞችህንም በከንቱ ይወስዷቸዋል።
21
አቤቱ፥ የሚጠሉህን እኔ የጠላሁ አይደለሁምን? ስለ ጠላቶችህም አልጠፋሁምን?
22
ፍጹም ጥልን ጠላኋቸው፥ ጠላቶችም ሆኑኝ።
23
አቤቱ፥ መርምረኝ፥ ልቤንም ፈትን፤ ፈትነኝ፥ መንገዶችንም ዕወቅ፤
24
በደልም በእኔ ላይ ቢገኝ እይ፤ የዘለዓለምንም መንገድ ምራኝ።
← Chapter 137
Chapter 139 →