bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Psalms 120
Psalms 120
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
1
ዐይኖቼን ወደ ተራሮች አነሣሁ፤ ረድኤቴ ከወዴት ይምጣ?
2
ረድኤቴ ሰማይና ምድርን ከፈጠረ ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው።
3
ለእግሮችህ ሁከትን አይሰጣቸውም፤ የሚጠብቅህም አይተኛም።
4
እነሆ፥ እስራኤልን የሚጠብቅ አይተኛም፥ አያንቀላፋምም።
5
እግዚአብሔር ይጠብቅህ፥ እግዚአብሔርም በቀኝ እጁ ይጋርድህ።
6
ፀሐይ በቀን አያቃጥልህ፤ ጨረቃም በሌሊት።
7
እግዚአብሔር ከክፉ ሁሉ ይጠብቅህ፥ እግዚአብሔር ነፍስህንም ይጠብቃት።
8
ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘለዓለም እግዚአብሔር መውጣትህንና መግባትህን ይጠብቅ።
← Chapter 119
Chapter 121 →