bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Psalms 121
Psalms 121
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
1
ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሂድ ስላሉኝ ደስ አለኝ።
2
ኢየሩሳሌም ሆይ፥ እግሮቻችን በአደባባዮችሽ ቆሙ።
3
ኢየሩሳሌምስ እንደ ከተማ የታነጸች ናት።
4
እንደ እርሷ ያሉት በአንድነት ከእርሷ ጋር ናቸው። አቤቱ፥ ለስምህ ይገዙ ዘንድ፥ ለእስራኤል ምስክር የሚሆኑ የእግዚአብሔር ወገኖች አሕዛብ ወደዚያ ይወጣሉና።
5
ለመፍረድ ዙፋኖቻቸውን በዚያ አስቀምጠዋልና፥ የዳዊት ቤት ዙፋኖች።
6
የኢየሩሳሌም ደኅንነትዋን፥ ተነጋገሩ። ስምህን ለሚወድዱ ደስታቸው ነው።
7
በኀይልህ ሰላም ይሁን፥ በክብርህ ቦታ ደስታ አለ።
8
ስለ ወንድሞቼና ስለ ባልንጀሮቼ ስለ አንቺም፥ ሰላምን ይናገራሉ።
9
ስለ አምላኬ ስለ እግዚአብሔር ቤት ደኅንነትሽን ፈለግሁ።
← Chapter 120
Chapter 122 →