bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Psalms 119
Psalms 119
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
1
አቤቱ፥ በተጨነቅሁ ጊዜ ወደ አንተ ጮኽሁ፥ ሰማኸኝም።
2
ከዐመፀኛ ከንፈር፥ ከሸንጋይም አንደበት፥ አቤቱ፥ ነፍሴን አድናት።
3
ስለ ሽንገላ አንደበት ምንን ይሰጡሃል? ምንስ ይጨምሩልሃል?
4
እንደ በረሃ ቋያ የኀያል ፍላጾች የተሳሉ ናቸው።
5
መኖሪያዬ የራቀ እኔ ወዮልኝ፤ በዘላን ድንኳኖች አደርሁ።
6
ሰላምን ከሚጠሉ ጋር ነፍሴ ብዙ ጊዜ ታገሠች።
7
እኔ ሰላማዊ ስሆን በተናገርኋቸው ጊዜ በከንቱ ይጠሉኛል።
← Chapter 118
Chapter 120 →