bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Psalms 12
Psalms 12
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
1
አቤቱ፥ እስከ መቼ ፈጽመህ ትረሳኛለህ? እስከ መቼስ ፊትህን ከእኔ ትመልሳለህ?
2
እስከ መቼ በነፍሴ ኀዘንን አኖራለሁ? እስከ መቼ ልቤ ሁልጊዜ ትጨነቅብኛለች? እስከ መቼ ጠላቶች በላዬ ይታበያሉ?
3
አቤቱ አምላኬ፥ ተመልከተኝ ስማኝም፤ ለሞትም እንዳያንቀላፉ ዐይኖቼን አብራቸው። ጠላቶቼም አሸነፍነው እንዳይሉ፥
4
የሚያስጨንቁኝም እኔ ብናወጥ ደስ እንዳይላቸው፥
5
እኔ ግን በቸርነትህ ታመንሁ፥ ልቤም በማዳንህ ደስ ይለዋል።
6
የረዳኝን እግዚአብሔርን አመሰግነዋለሁ፤ ለልዑል እግዚአብሔር ስምም እዘምራለሁ።
← Chapter 11
Chapter 13 →