bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Psalms 13
Psalms 13
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
1
ሰነፍ በልቡ፥ “እግዚአብሔር የለም” ይላል። በሥራቸው ረከሱ፥ ጐሰቈሉም፤ በጎ ነገርን የሚሠራት የለም። አንድም እንኳ የለም።
2
የሚያስተውል፥ እግዚአብሔርንም የሚፈልግ እንዳለ ያይ ዘንድ እግዚአብሔር ከሰማይ የሰው ልጆችን ተመለከተ።
3
ሁሉ ተስተካክሎ በአንድነት ዐመፀ፤ በጎ ነገርን የሚሠራት የለም፤ አንድም እንኳ የለም።
4
ጕሮሮኣቸው እንደ መቃብር የተከፈተ ነው፥ በምላሳቸው ሸነገሉ፤
5
ከከንፈራቸው በታች የእባብ መርዝ አለ፤ አፋቸው መራራ ነው፥ መርገምንም ተሞልቶአል፤
6
ደምን ለማፍሰስ እግራቸው ፈጣን ነው፤ ጥፋትና ጕስቍልና በመንገዳቸው አለ፥ የሰላምን መንገድ አላወቁአትምና፤ እግዚአብሔርን መፍራት በዐይናቸው ፊት የለም።
7
ሕዝቤን እንደ እንጀራ የሚበሉ፥ ኀጢአትን የሚሠሩ ሁሉ አያውቁም። እግዚአብሔርንም አይጠሩትም።
8
በዚያም ፈሩ፥ የማያስፈራውም አስፈራቸው። እግዚአብሔር በጻድቃን ትውልድ ዘንድ ነውና።
9
የድሆችን ምክር አሳፈራችሁ፥ እግዚአብሔር ግን ተስፋቸው ነው።
10
ከጽዮን መድኀኒትን ለእስራኤል ማን ይሰጣል? እግዚአብሔር የሕዝቡን ምርኮ በመለሰ ጊዜ፥ ያዕቆብ ደስ ይለዋል፥ እስራኤልም ሐሤትን ያደርጋል።
← Chapter 12
Chapter 14 →