bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Psalms 11
Psalms 11
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
1
አቤቱ፥ አድነኝ፥ ደግ ሰው አልቆአልና፥ ከሰው ልጆችም መተማመን ጐድሎአልና።
2
እርስ በርሳቸው ከንቱ ነገርን ይናገራሉ፤ በሽንገላ ከንፈር ሁለት ልብ ሆነው ይናገራሉ።
3
የሽንገላን ከንፈሮች ሁሉ እግዚአብሔር ያጠፋቸዋል፥ ታላቅ ነገርን የምትናገረውንም ምላስ፤
4
“ምላሳችንን እናበረታለን፤ ከንፈሮቻችን የእኛ ናቸው፥ ጌታችን ማን ነው?” የሚሉትን።
5
“ስለ ድሆች መከራ፥ ስለ እስረኞችም ጩኸት እግዚአብሔር ይላል፥ አሁን እነሣለሁ፤ መድኀኒትን አደርጋለሁ፥ በእርሱም እገልጣለሁ።”
6
በምድር ላይ እንደ ተፈተነ፥ ሰባት ጊዜም እንደ ተጣራ ብር የእግዚአብሔር ቃል ንጹሕ ቃል ነው።
7
አቤቱ፥ አንተ ጠብቀን፥ ከዚህችም ትውልድ ለዘለዓለም ታደገን።
8
ዝንጉዎች በዙሪያው ይመላለሳሉ። እንደ ገናናነትህ መጠን የሰው ልጆችን አጸናሃቸው።
← Chapter 10
Chapter 12 →