bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Psalms 118
Psalms 118
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
1
በመንገዳቸው ንጹሓን የሆኑ፥ በእግዚአብሔርም ሕግ የሚሄዱ ብፁዓን ናቸው።
2
ምስክሩን የሚፈልጉ፥ በፍጹም ልብ የሚሹት ብፁዓን ናቸው፤
3
ዐመፃን የሚያደርጉ ግን በመንገዱ አይሄዱም።
4
ትእዛዛትህን እጅግ ይጠብቁ ዘንድ አንተ አዘዝህ።
5
ሥርዐትህን እጠብቅ ዘንድ የሚቀናስ ከሆነ መንገዴ ይቅና።
6
ትእዛዝህን ሁሉ ስመለከት በዚያን ጊዜ አላፍርም።
7
አቤቱ፥ የጽድቅህን ፍርድ ስማር በቅን ልብ አመሰግንሃለሁ።
8
ሥርዐትህንም እጠብቃለሁ፤ ለዘለዓለም አትጣለኝ።
9
ጐልማሳ መንገዱን በምን ያቀናል? ቃልህን በመጠበቅ ነው።
10
በፍጹም ልቤ ፈለግሁህ፥ ከትእዛዝህ አታርቀኝ።
11
አንተን እንዳልበድል፥ ቃልህን በልቤ ሰወርሁ።
12
አቤቱ፥ አንተ ቡሩክ ነህ፤ ሥርዐትህንም አስተምረኝ።
13
የአፍህን ፍርድ ሁሉ በከንፈሬ ነገርሁ።
14
እንደ ብልጥግና ሁሉ በምስክርህ መንገድ ደስ አለኝ።
15
ትእዛዝህን አሰላሰልሁ፥ መንገድህንም እፈልጋለሁ።
16
ትእዛዞችህን አነብባለሁ፤ ቃልህንም አልረሳም።
17
ሕያው እንድሆን ቃልህንም እንድጠብቅ ለባሪያህ ስጠው።
18
ዓይኖችን ክፈት፥ ከሕግህም ድንቅ ነገርን አያለሁ።
19
እኔ በምድር ስደተኛ ነኝ፤ ትእዛዛትህን ከእኔ አትሰውር።
20
ነፍሴ ሁልጊዜ ፍርድህን እጅግ ናፈቀች። ትዕቢተኞችን ገሠጽኻቸው፥
21
ከትእዛዛትህ የሚርቁ ርጉማን ናቸው።
22
ትእዛዝህን ፈልጌአለሁና ስድብንና ነውርን ከእኔ አርቅ።
23
አለቆች ደግሞ ተቀምጠው እኔን አሙኝ፤ ባሪያህ ግን ፍርድህን ያሰላስል ነበር።
24
ምስክርህም ትምህርቴ ነው፥ ሥርዐትህም መካሬ ነው።
25
ሰውነቴ ወደ ምድር ተጣበቀች፤ እንደ ቃልህ ሕያው አድርገኝ።
26
መንገድህንና ምስክርህን ነገርሁ፥ ፍርድህን አስተምረኝ።
27
የእውነትህን መንገድ እንዳስተውል አድርገኝ፥ ተአምራትህንም አሰላስላለሁ።
28
ከኀዘን የተነሣ ሰውነቴ አንቀላፋች፤ በቃልህ አጠንክረኝ።
29
የዐመፃን መንገድ ከእኔ አርቅ፥ በሕግህም ይቅር በለኝ፤
30
የእውነትህን መንገድ መረጥሁ፥ ፍርድህንም አልረሳሁም።
31
አቤቱ፥ ምስክርህን ተከተልሁ፥ አታሳፍረኝ።
32
ልቤን ባሰፋኸው ጊዜ፥ በትእዛዝህ መንገድ ሮጥሁ።
33
አቤቱ፥ የእውነትህን መንገድ አስተምረኝ፥ ሁልጊዜም እፈልጋታለሁ።
34
እንዳስተውል አድርገኝ፥ ሕግህንም እፈልጋለሁ፤ በፍጹም ልቤም እጠብቀዋለሁ።
35
እርስዋን ወድጃለሁና የትእዛዝህን መንገድ ምራኝ።
36
ልቤን ወደ ምስክርህ መልስ፥ ወደ ቅሚያም አይሁን።
37
ከንቱ ነገርን እንዳያዩ ዐይኖቼን መልስ፤ በመንገድህም ሕያው አድርገኝ።
38
እንዲፈራህ ለባሪያህ በቃልህ የተናገርኸውን አጽና።
39
ፍርድህ መልካም ነውና የተጠራጠርሁትን ስድብ ከእኔ አርቅ።
40
እነሆ፥ ትእዛዝህን ናፈቅሁ፥ በጽድቅህም ሕያው አድርገኝ።
41
አቤቱ፥ ምሕረትህ ይምጣልኝ፥ አቤቱ፥ ማዳንህ እንደ ቃልህ ነው።
42
በቃልህ ታምኛለሁና ለሚሰድቡኝ በነገር እመልስላቸዋለሁ።
43
በፍርድህም ታምኛለሁና የእውነትን ቃል ከአፌ ፈጽመህ አታርቅ።
44
ለዘለዓለም ዓለም ሁልጊዜ ሕግህን እጠብቃለሁ።
45
ትእዛዛትህንም ፈልጌአለሁና አስፍቼ እሄዳለሁ።
46
በነገሥታት ፊት ምስክርህን እናገራለሁ፥ አላፍርምም፤
47
እጅግም የወደድኋቸውን ትእዛዛትህን እናገራለሁ።
48
እጆቼንም ወደ ወደድኋቸው ወደ ትእዛዛትህ አነሣለሁ፤ ፍርድህንም አሰላስላለሁ።
49
ለባሪያህ ተስፋ ያስደረግኸውን ቃልህን አስብ።
50
ቃልህ ሕያው አድርጎኛልና። ይህች በመከራዬ ደስ አሰኘችኝ።
51
ትዕቢተኞች እጅግ ዐመፁ፤ እኔ ግን ከሕግህ አልራቅሁም።
52
ከጥንት የነበረውን ፍርድህን ዐሰብሁ፥ አቤቱ፥ደስ አለኝ።
53
ሕግህን ከተዉ ኃጥኣን የተነሣ ኀዘን ያዘኝ።
54
በእንግድነቴ ሀገር ፍርድህ መዝሙር ሆነኝ።
55
አቤቱ፥ በሌሊት ስምህን ዐሰብሁ፥ ሕግህንም ጠበቅሁ።
56
ትእዛዛትህንም ፈልጌአለሁና ይህች ሆነችልኝ።
57
እግዚአብሔር ክፍሌ ነው፤ ሕግህን ይጠብቁ አልሁ።
58
አቤቱ በፍጹም ልቤ ወደ ፊትህ ለመንሁ፤ እንደ ቃልህ ይቅር በለኝ።
59
ስለ መንገዶችህ ዐሰብሁ፥ እግሬንም ወደ ምስክርህ መለስሁ።
60
ትእዛዝህን ለመጠበቅ ጨከንሁ፥ አልተጠራጠርሁምም።
61
የኃጥኣን ገመዶች ተተበተቡብኝ፤ ሕግህን ግን አልረሳሁም።
62
ስለ ጽድቅህ ፍርድ፥ አመሰግንህ ዘንድ በእኩለ ሌሊት እነሣለሁ።
63
እኔ ለሚፈሩህ ሁሉ፥ ትእዛዝህንም ለሚጠብቁ ባልንጀራ ነኝ።
64
አቤቱ፥ ይቅርታህ በምድር ሁሉ ሞላች፤ ሥርዐትህንም አስተምረኝ።
65
አቤቱ፥ እንደ ቃልህ ለባሪያህ መልካም አደረግህ።
66
በትእዛዛትህ ታምኛለሁና መልካም ምክርንና ጥበብን አስተምረኝ።
67
እኔ ሳልጨነቅ ተጸጸትሁ፤ ስለዚህም ቃልህን ጠበቅሁ።
68
አቤቱ፥ አንተ ቸር ነህ፥ በቸርነትህም ፍርድህን አስተምረኝ።
69
የትዕቢተኞች ዐመፃ በላዬ በዛ፤ እኔ ግን በፍጹም ልቤ ትእዛዛትህን እፈልጋለሁ።
70
ልባቸው እንደ ወተት ረጋ፤ እኔ ግን ሕግህን አነብባለሁ
71
ፍርድህን አውቅ ዘንድ ያስጨነቅኸኝ መልካም ሆነልኝ።
72
ከአእላፋት ወርቅና ብር ይልቅ። የአፍህ ሕግ ይሻለኛል።
73
እጆችህ ሠሩኝ፥ አበጃጁኝም፤ እንዳስተውል አድርገኝ፥ ትእዛዛትህንም እማራለሁ።
74
በቃልህ ታምኛለሁና የሚፈሩህ እኔን አይተው ደስ ይላቸዋል።
75
አቤቱ፥ ፍርድህ ጽድቅ እንደ ሆነች፥ በሚገባም እንዳስጨነቅኸኝ ዐወቅሁ።
76
ምሕረትህ ለደስታዬ ይሁነኝ፥ እንደ ቃልህም ለባሪያህ ይሁነው።
77
ሕግህ ትምህርቴ ነውና ቸርነትህ ይምጣልኝ፥ በሕይወትም ልኑር።
78
ትዕቢተኞች ዐመፃን መክረውብኛልና ይፈሩ፤ እኔ ግን ትእዛዝህን አሰላስላለሁ።
79
የሚፈሩህና ምስክሮችህን የሚያውቁ ወደ እኔ ይመለሱ።
80
እንዳላፍር ልቤ በፍርድህ ንጹሕ ይሁን።
81
ነፍሴ ወደ ማዳንህ አለፈች፤ በቃልህም ታመንሁ።
82
መቼ ታጽናናኛለህ እያልሁ ዐይኖቼ ትድግናህን በመጠበቅ ፈዘዙ።
83
በውርጭ እንዳለ ረዋት ሆኛለሁና፤ ፍርድህን ግን አልረሳሁም።
84
የባሪያህ ዘመኖች ምን ያህል ናቸው? በሚያሳድዱኝስ ላይ መቼ ትፈርድልኛለህ?
85
ኃጥኣን ዋዛ-ፈዛዛን ነገሩኝ፥ አቤቱ፥ እንደ ሕግህ ግን አይደለም።
86
ትእዛዝትህ ሁሉ እውነት ናቸው፤ በዐመፃ አሳድደውኛል፤ ርዳኝ።
87
ከምድር ሊያጠፉኝ ጥቂት ቀርቶአቸው ነበር፤ እኔ ግን ትእዛዛትህን አልተውሁም።
88
እንደ ምሕረትህ ሕያው አድርገኝ፤ የአፍህንም ምስክር እጠብቃለሁ። ላሜድ።
89
አቤቱ፥ ቃልህ በሰማይ ለዘለዓለም ይኖራል።
90
እውነትህ ለልጅ ልጅ ናት፤ ምድርን መሠረትሃት፥ እርስዋም ትኖራለች።
91
ሁሉን ገዝተሃልና ቀኑ በትእዛዝህ ይኖራል።
92
ሕግህ ትምህርቴ ባይሆን፥ ቀድሞ በጕስቍልናዬ በጠፋሁ ነበር።
93
በእርሱ ሕያው አድርገኸኛልና ፍርድህን ለዘለዓለም አልረሳም።
94
እኔ የአንተ ነኝ፥ ፍርድህን ፈልጌአለሁና አድነኝ።
95
ኃጥኣን ያጠፉኝ ዘንድ ጠበቁኝ፤ ምስክርህን አስተውያለሁና።
96
የሥራውን ሁሉ ፍጻሜ አየሁ፤ ትእዛዝህ ግን እጅግ ሰፊ ነው።
97
አቤቱ፥ ሕግህን እንደምን እጅግ ወደድሁ! ቀኑን ሁሉ እርሱ ትምህርቴ ነው።
98
ለዘለዓለም ለእኔ ነውና ትእዛዝህ ከጠላቶቼ ይልቅ አስተዋይ አደረገኝ።
99
ትእዛዝህ ትምህርቴ ነውና ካስተማሩኝ ሁሉ ይልቅ አስተዋልሁ።
100
ትእዛዝህን ፈልጌአለሁና ከሽማግሌዎች ይልቅ አስተዋልሁ።
101
ቃልህን እጠብቅ ዘንድ ከክፉ መንገድ ሁሉ እግሬን ከለከልሁ።
102
አንተ አስተምረኸኛልና ከፍርድህ አልራቅሁም።
103
ቃልህ ለጕሮሮዬ ጣፋጭ ነው፤ ከማርና ከወለላ ይልቅ ለአፌ ጣፈጠኝ።
104
ከትእዛዝህ የተነሣ አስተዋልሁ፤ ስለዚህ የዐመፃን መንገድ ጠላሁ።
105
ሕግህ ለእግሬ መብራት፥ ለመንገዴም ብርሃን ነው።
106
የጽድቅህን ፍርድ እጠብቅ ዘንድ ማልሁ፥ አጸናሁም።
107
እጅግ መከራ ተቀበልሁ፥ አቤቱ፥ እንደ ቃልህ ሕያው አድርገኝ።
108
አቤቱ፥ ከአፌ የሚወጣውን ቃል ውደድ፥ ፍርድህንም አስተምረኝ።
109
ነፍሴ ሁልጊዜ በእጅህ ውስጥ ናት፤ ሕግህን ግን አልረሳሁም።
110
ኃጥኣን ወጥመድን ዘረጉብኝ፤ ከትእዛዝህ ግን አልሳትሁም።
111
የልቤ ደስታ ነውና ምስክርህን ለዘለዓለም ወረስሁ።
112
ለዘለዓለም ያለ ነቀፋ ትእዛዝህን አደርግ ዘንድ ልቤን መለስሁ።
113
ዐመፀኞችን ጠላሁ፥ ሕግህን ግን ወደድሁ።
114
አንተ ረዳቴና መጠጊያዬ ነህ፥ በቃልህም ተማመንሁ።
115
እናንተ ዐመፀኞች፥ ከእኔ ራቁ፥ የአምላኬንም ትእዛዝ ልፈልግ።
116
እንደ ቃልህ ተቀበለኝ፥ ሕያውም እሆናለሁ፤ ከተስፋዬም አታሳፍረኝ።
117
ርዳኝም፥ አድነኝም፥ ሁልጊዜም ፍርድህን አነብባለሁ።
118
ምኞታቸው ዐመፃ ነውና ከሥርዐትህ የሚርቁትን ሁሉ አጐሳቈልሃቸው።
119
የምድር ኃጥኣን ሁሉ ወንጀለኞች ናቸው፤ ስለዚህ ምስክርህን ወደድሁ።
120
መፈራትህን በሥጋዬ ውስጥ አስማማ፤ ከፍርድህ የተነሣ ፈርቻለሁና።
121
ፍርድንና ጽድቅን ሠራህ፤ ለሚያስጨንቁኝ አሳልፈህ አትስጠኝ።
122
ባሪያህን በመልካም ጠብቀው፤ ትዕቢተኞችም አይጋፉኝ።
123
ዐይኖቼ ለማዳንህ፥ ለጽድቅህም ቃል ፈዘዙ።
124
ለባሪያህ እንደ ምሕረትህ አድርግ፥ ፍርድህንም አስተምረኝ።
125
እኔ ባሪያህ ነኝ፤ እንዳስተውል አድርገኝ፥ ምስክርህንም አውቃለሁ።
126
ለእግዚአብሔር የሥራ ጊዜ አለው፥ ሕግህንም ሻሩት።
127
ስለዚህ ከወርቅና ከዕንቍ ይልቅ ትእዛዝህን ወደድሁ።
128
ስለዚህ ወደ ትእዛዝህ ሁሉ አቀናሁ፥ የዐመፃንም መንገድ ሁሉ ጠላሁ።
129
ምስክርህ ድንቅ ነው፤ ስለዚህ ነፍሴ ፈለገችው።
130
የቃልህ ነገር ያበራል፥ ሕፃናትንም አስተዋዮች ያደርጋል።
131
አፌን ከፈትሁ፥ ልቡናዬንም አሰፋሁ፤ ትእዛዝህን ወድጃለሁና።
132
ስምህን ለሚወድዱ እንደምታደርገው ፍርድ፥ ወደ እኔ ተመልከት፥ ይቅርም በለኝ።
133
መንገዴንና አካሄዴን እንደ ቃልህ አቅና፤ ኀጢአትም ሁሉ ድል አይንሳኝ።
134
ከሰው ቅሚያ አድነኝ፤ ትእዛዝህንም እጠብቃለሁ ።
135
በባሪያህ ላይ ፊትህን አብራ፥ ፍርድህንም አስተምረኝ።
136
ሕግህን አልጠበቅሁምና የውኃ ፈሳሽ ከዐይኖች ፈሰሰ።
137
አቤቱ፥ አንተ ጻድቅ ነህ፥ ፍርድህም ቅን ነው።
138
ምስክርህን በጽድቅ አዘዝህ፥ እጅግም ቅን ነው።
139
ጠላቶቼ ትእዛዝህን ረስተዋልና የቤትህ ቅንዓት አቀለጠኝ።
140
ቃልህ እጅግ የጋለ ነው፥ ባሪያህ ግን ወደደው።
141
እኔ ታናሽና የተናቅሁ ነኝ፥ ሕግህን ግን አልረሳሁም።
142
ጽድቅህም የዘለዓለም ጽድቅ ነው፥ ቃልህም የታመነ ነው።
143
መከራና ችግር አገኙኝ፤ ትእዛዝህ ግን ትምህርቴ ነው።
144
ምስክርህ ለዘለዓለም እውነት ነው፤ እንዳስተውል አድርገኝ፥ በሕይወትም አኑረኝ።
145
በፍጹም ልቤ ጮኽሁ፥ አቤቱ ስማኝ፤ ፍርድህንም ፈለግሁ።
146
ወደ አንተ ጮኽሁ፥ ስማኝ አድነኝም። ምስክርህንም ልጠብቅ።
147
ወደ ተራሮች ደረስሁ፥ ጮኽሁም። ቃልህን ተስፋ አድርጌአለሁና።
148
ዐይኖቼ ለመማለድ ደረሱ፥ ቃልህን እናገር ዘንድ።
149
አቤቱ፥ እንደ ይቅርታህ ቃሌን ስማ፤ እንደ ፍርድህ ሕያው አድርገኝ።
150
በዐመፃ የከበቡኝ ቀረቡ፥ ከሕግህ ግን ራቁ።
151
አቤቱ አንተ ቅርብ ነህ፥ መንገዶችህም ሁሉ የቀኑ ናቸው።
152
ለዘለዓለም እንደ መሠረትሃቸው ከቀድሞ ጀምሮ ምስክሮችህን ዐወቅሁ።
153
ሕግህን አልረሳሁምና ችግሬን ተመልከት፥ አድነኝም።
154
ፍርዴን ፍረድ አድነኝም፤ ስለ ቃልህም ሕያው አድርገኝ።
155
ሕይወት ከኃጥኣን የራቀ ነው፥ ፍርድህን አልፈለጉምና።
156
አቤቱ፥ ይቅርታህ እጅግ የበዛ ነው፤ እንደ ፍርድህም ሕያው አድርገኝ።
157
የከበቡኝና ያስጨነቁኝ ብዙዎች ናቸው፤ ከምስክርህ ግን ፈቀቅ አላልሁም።
158
ቃልህን አልጠበቁምና ሰነፎችን አይቼ አዘንሁ።
159
ትእዛዝህን እንደ ወደድሁ ተመልከት፤ አቤቱ፥ በይቅርታህ ሕያው አድርገኝ።
160
የቃልህ መጀመሪያ እውነት ነው፥ ፍርድህም ሁሉ ለዘለዓለም እውነት ነው።
161
አለቆች በከንቱ አሳደዱኝ፤ ከቃልህ የተነሣ ግን ልቤ ደንገጠብኝ።
162
ብዙ ምርኮ እንዳገኘ በቃልህ ደስ አለኝ።
163
ዐመፃን ጠላሁ ተጸየፍሁም፤ ሕግህን ግን ወደድሁ።
164
ስለ እውነት ፍርድህ ሰባት ጊዜ በቀን አመሰግንሃለሁ።
165
ስምህን ለሚወድዱ ብዙ ሰላም ነው፥ ዕንቅፋት የለባቸውም።
166
አቤቱ፥ ማዳንህን ተስፋ አደረግሁ፥ ትእዛዛትህንም ጠበቅሁ።
167
ነፍሴ ምስክርህን ጠበቀች፥ እጅግም ወደደችው።
168
አቤቱ፥ መንገዶችህ ሁሉ በፊትህ ናቸውና። ትእዛዝህንና ምስክርህን ጠበቅሁ።
169
አቤቱ፥ ልመናዬ ወደ አንተ ትቅረብ፤ እንደ ቃልህም አስተዋይ አድርገኝ።
170
አቤቱ፥ ምልጃዬ ወደ ፊትህ ትድረስ፤ እንደ ቃልህም አድነኝ።
171
ፍርድህን አስተምረኸኛልና ከንፈሮች ምስጋናህን ይናገራሉ።
172
ትእዛዛትህ ሁሉ ጽድቅ ናቸውና፥ አንደበቴ ቃልህን ተናገረ።
173
ትእዛዛትህን ወድጃለሁና ቀኝህ የሚያድነኝ ይሁን።
174
አቤቱ፥ ማዳንህን ናፈቅሁ፤ ሕግህም ትምህርቴ ነው።
175
ነፍሴ ትኑርልኝ ላመስግንህም፥ ፍርድህም ይርዳኝ።
176
እንደ ጠፋ በግ ተዘነጋሁ፤ ትእዛዛትህን አልረሳሁምና ባሪያህን ፈልገው።
← Chapter 117
Chapter 119 →