bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Psalms 111
Psalms 111
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
1
እግዚአብሔርን የሚፈራ፥ ትእዛዙንም እጅግ የሚወድድ ሰው ብፁዕ ነው።
2
ዘሩ በምድር ላይ ኀያል ይሆናል፤ የጻድቃን ትውልዶች ይባረካሉ።
3
ክብርና ባለጠግነት በቤቱ ነው፥ ጽድቁም ለዘለዓለም ይኖራል።
4
ለቅኖች ብርሃን በጨለማ ወጣ፤ እግዚአብሔር መሓሪና ይቅር ባይ ነው፤ አምላካችንም ጻድቅ ነው።
5
ርኅሩኅ፥ ይቅር ባይና ቸር ሰው ነገሩን በፍርድ ይፈጽማል።
6
ለዘለዓለም አይታወክም፤ የጻድቅ መታሰቢያ ለዘለዓለም ይኖራል።
7
ከክፉ ነገርም አይፈራም፤ በእግዚአብሔር ለመታመን ልቡ የጸና ነው።
8
በጠላቶቹ ላይ እስኪያይ ድረስ ልቡ ጽኑዕ ነው፥ ለዘለዓለምም አይታወክም።
9
በተነ፥ ለችግረኞችም ሰጠ፤ ጽድቁ ለዘለዓለም ዓለም ይኖራል፤ ቀንዱም በክብር ከፍ ከፍ ይላል።
10
ኀጢአተኛም አይቶ ይቈጣል፥ ጥርሱንም ያፋጫል፥ ይቀልጣልም፤ የኃጥኣንም ምኞት ትጠፋለች።
← Chapter 110
Chapter 112 →