bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Psalms 112
Psalms 112
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
1
የእግዚአብሔር ባሪያዎች ሆይ፥ አመስግኑት፥ የእግዚአብሔርን ስም አመስግኑ።
2
ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘለዓለም ድረስ የእግዚአብሔር ስሙ ቡሩክ ይሁን።
3
ከፀሐይ መውጫ ጀምሮ እስከ መግቢያው ድረስ የእግዚአብሔር ስሙ ይመስገን።
4
እግዚአብሔር በአሕዛብ ሁሉ ላይ ልዑል ነው፥ ክብሩም ከሰማያት በላይ ነው።
5
እንደ አምላካችን እንደ እግዚአብሔር ማን ነው? በልዕልና የሚኖር።
6
በሰማይና በምድር የተዋረዱትን የሚያይ፤
7
ድሃውን ከምድር የሚያነሣ፥ ምስኪኑንም ከመሬት ከፍ ከፍ የሚያደርግ፤
8
ከአለቆች ጋር ከሕዝቡም አለቆች ጋር ያኖረው ዘንድ
9
መካኒቱን በቤቱ የሚያኖራት፥ ደስ የተሰኘችም የልጆች እናት የሚያደርጋት።
← Chapter 111
Chapter 113 →