bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Psalms 110
Psalms 110
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
1
አቤቱ፥ በቅኖች ሸንጎ በጉባኤም በፍጹም ልቤ አመሰግንሃለሁ።
2
የእግዚአብሔር ሥራ ታላቅ ናት፥ በፈቃዱም ሁሉ የተፈለገች ናት።
3
ሥራው ምስጋናና የጌትነት ክብር ነው። ጽድቁም ለዘለዓለም ይኖራል።
4
ለጌትነቱ መታሰቢያን አደረገ፤ እግዚአብሔር መሓሪና ይቅር ባይ ነው።
5
ለሚፈሩት ምግብን ሰጣቸው፤ ኪዳኑንም ለዘለዓለም ያስባል።
6
የአሕዛብን ርስት ይሰጣቸው ዘንድ ለሕዝቡ የሥራውን ብርታት አሳየ።
7
የእጆቹ ሥራ እውነትና ቅን ነው፤ ትእዛዙም ሁሉ የታመነ ነው፥
8
ለዘለዓለምም የጸና ነው፥ በእውነትና በቅንም የተሠራ ነው።
9
እግዚአብሔርም መድኀኒትን ለሕዝቡ ላከ፥ ኪዳኑንም ለዘለዓለም አዘዘ፤ ስሙ የተቀደሰና የተፈራ ነው።
10
የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው፥ ለሚያደርጋት ሁሉ ምክር መልካም ናት ምስጋናውም ለዘለዓለም ይኖራል።
← Chapter 109
Chapter 111 →