bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Psalms 109
Psalms 109
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
1
ጌታ ጌታዬን፥ “ጠላቶችህን ለእግርህ መረገጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ” አለው።
2
እግዚአብሔር የኀይልን በትር ከጽዮን ይልክልሃል፤ በጠላቶችህም መካከል ትገዛለህ።
3
ቀዳማዊ፦ በኀይል ቀን፥ በቅዱሳን ብርሃን ከአንተ ጋር ነበር፥ ከአጥቢያ ኮከብ አስቀድሞ ከሆድ ወለድሁህ።
4
እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት አንተ ለዘለዓለም ካህን ነህ ብሎ፥ እግዚአብሔር ማለ አይጸጸትምም።
5
እግዚአብሔር በቀኝህ ነው፥ ነገሥታትን በቍጣው ቀን ይቀጠቅጣቸዋል።
6
በአሕዛብ መካከል ይፈርዳል፥ ሬሳዎችንም ያበዛል፤ በምድር ላይ የብዙዎችን ራሶች ይቀጠቅጣል።
7
በመንገድ ከፈሳሽ ውኃ ጠጡ፤ ስለዚህ ራስ ከፍ ከፍ ይላል።
← Chapter 108
Chapter 110 →