bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Psalms 108
Psalms 108
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
1
አቤቱ፥ ልመናዬን ቸል አትበል፥
2
የዐመፀኛ አፍና የኀጢአተኛ አፍ በላዬ ተላቅቀዋልና። በሽንገላ አንደበትም በላዬ ተናገሩ፤
3
በጥል ከበቡኝ፥ በከንቱም ተዋጉኝ።
4
በወደድኋቸው ፋንታ አጣሉኝ፥ እኔ ግን እጸልያለሁ።
5
በመልካም ፋንታ ክፉን ከፈሉኝ። በወደድኋቸውም ፋንታ ጠሉኝ።
6
በላዩ ኀጢአተኛን ሹም፤ ሰይጣንም በቀኙ ይቁም።
7
በሚከራከርም ጊዜ ተረትቶ ይውጣ፤ ጸሎቱም በደል ትሁንበት።
8
ዘመኖቹም ጥቂት ይሁኑ፤ ሹመቱንም ሌላ ይውሰድ።
9
ልጆቹም ድሃ አደጎች ይሁኑ፥ ሚስቱም መበለት ትሁን።
10
ልጆቹም ታውከው ይሰደዱ፥ ይለምኑም፥ ከቤቶቻቸውም ያባርሯቸው።
11
ባለ ዕዳም ገንዘቡን ሁሉ ይበርብረው፥ የደከመበትንም ሁሉ ባዕድ ይበዝብዘው።
12
የሚረዳውንም አያግኝ፤ ለድሃ አደግ ልጆቹም የሚራራ አይኑር።
13
ልጆቹም ይጥፉ፤ በአንዲት ትውልድ ስሙ ትጥፋ።
14
የአባቱ ኀጢአት በእግዚአብሔር ፊት ትታሰብ፤ የእናቱም ኀጢአት አይደምሰስ።
15
በእግዚአብሔርም ፊት ሁልጊዜ ይኑር፤ መታሰቢያውም ከምድር ይጥፋ።
16
ምጽዋትን ያደርግ ዘንድ አላሰበምና ድሃንና ምስኪንንም ሰው አሳዷልና ልቡም ሰውን ለመግደል የጨከነ ነውና።
17
መርገምን መረጣት፥ ወደ እርሱም ትምጣ፤ በረከትንም አልመረጣትም ከእርሱም ትራቅ።
18
መርገምን እንደ ልብስ ለበሳት፥ እንደ ውኃም ወደ አንጀቱ፥ እንደ ቅባትም ወደ አጥንቱ ገባች።
19
እንደሚለብሰው ልብስ፥ ሁልጊዜም እንደሚታጠቀው ትጥቅ ትሁነው።
20
ይህ ሥራ በእግዚአብሔር ዘንድ በሚያጣሉኝ በነፍሴም ላይ ክፉን በሚናገሩ ነው።
21
አንተ ግን አቤቱ፥ ጌታዬ፥ ስለ ስምህ ምሕረትህን በእኔ ላይ አድርግ፤ ምሕረትህ መልካም ናትና አድነኝ።
22
እኔ ድሃና ምስኪን ነኝና፥ ልቤም በውስጤ ደነገጠብኝ።
23
እንዳለፈ ጥላ አለቅሁ፥ እንደ አንበጣም ረገፍሁ።
24
ጕልበቶች በጾም ደከሙ፤ ሥጋዬም ቅባት በማጣት ከሳ።
25
እኔም በእነርሱ ዘንድ ተሰደብሁ፤ ባዩኝ ጊዜም ራሳቸውን ነቀነቁ።
26
አቤቱ፥ አምላኬ፥ ርዳኝ፥ ስለ ምሕረትህም አድነኝ።
27
አቤቱ፥ እጅህ ይህች እንደ ሆነች፥ አንተም ይህችን እንዳደረግህ ይወቁ።
28
እነርሱ ይራገማሉ፥ አንተ ግን ባርክ፤ በእኔ ላይ የሚነሡም ይፈሩ፥ ባሪያህ ግን ደስ ይበለው።
29
የሚያጣሉኝ እፍረትንና ውርደትን ይልበሱ፤ ኀጢአታቸውን እንደ መጐናጸፊያ ይልበሱአት።
30
እግዚአብሔርን በአፌ እጅግ አመሰግነዋለሁ። በብዙዎችም መካከል አከብረዋለሁ።
31
ነፍሴን ከሚከብቡአት ያድን ዘንድ በእኔ በድሃው ቀኝ ቆሞአልና።
← Chapter 107
Chapter 109 →