bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Psalms 107
Psalms 107
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
1
ልቤ ጽኑዕ ነው፥ አቤቱ፥ ልቤ ጽኑዕ ነው፤ አመሰግናለሁ እዘምራለሁም።
2
ክብሬም ይመለስልኛል፥ በበገናና በመሰንቆ እነሣለሁ፤ ማልጄም እነሣለሁ፤
3
አቤቱ፥ በአሕዛብ መካከል አመሰግንሃለሁ፤ በወገኖችም መካከል እዘምርልሃለሁ፤
4
ምሕረትህ በሰማይ ላይ ታላቅ ናትና፥ እውነትህም እስከ ደመናት ድረስ ነውና።
5
እግዚአብሔርም በሰማያት ላይ ከፍ ከፍ አለ፥ ክብሩም በምድር ሁሉ ላይ ነው።
6
ወዳጆችህ ይድኑ ዘንድ በቀኝህ አድን፥ አድምጠኝም።
7
እግዚአብሔር በመቅደሱ ተናገረ፥ ደስ ይለኛል፥ ሰቂማንም እካፈላለሁ፥ የሸለቆ ቦታዎችን እሰፍራለሁ።
8
ገለዓድ የእኔ ነው፥ ምናሴም የእኔ ነው፤ ኤፍሬም የራሴ መጠጊያ ነው። ይሁዳ ንጉሤ ነው፤
9
ካህን ሞዓብም ተስፋዬ ነው፥ በኤዶምያስ ላይም ጫማዬን እዘረጋለሁ፤ ፍልስጥኤምም ይገዙልኛል።
10
ወደ ጽኑ ከተማ ማን ይወስደኛል? ማንስ እስከ ኤዶምያስ ይመራኛል?
11
አቤቱ፥ የጣልኸን አንተ አይደለህምን? አምላካችን ሆይ፥ ከሠራዊታችን ጋር አትወጣም።
12
በመከራችን ረድኤትን ስጠን፤ በሰውም መታመን ከንቱ ነው።
13
በእግዚአብሔር ኀይልን እናደርጋለን፤ እርሱም የሚያስጨንቁንን ያዋርዳቸዋል።
← Chapter 106
Chapter 108 →