bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
/
Song of Solomon 8
Song of Solomon 8
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
1
ምነው አንተ የእናቴን ጡት እንደ ጠባ እንደ ወንድሜ በሆንክልኝ፤ በመንገድ ላይ አግኝቼ ብስምህ ማንም ሰው አይንቀኝም ነበር፤
2
ወደ ወላጅ እናቴ ቤት ባስገባሁህ ነበር፤ በዚያም ስለ ፍቅር ባስተማርከኝ ነበር፤ በሮማን ፍሬዬ ጭማቂ የጣፈጠውን መልካሙን የወይን ጠጅ ባጠጣሁህ ነበር።
3
ግራ እጁን ያንተርሰኛል፤ በቀኝ እጁ ያቅፈኛል።
4
እናንተ የኢየሩሳሌም ቈነጃጅ ሆይ! ፍቅር ራሱ ወዶ እስኪነሣ ድረስ ቀስቅሳችሁ እንዳታስነሡት ዐደራ እላችኋለሁ።
5
በወዳጅዋ ትከሻ ላይ ደገፍ ብላ ከበረሓ የምትመጣ ይህች ማን ናት? ዱሮ እናትህ አንተን አምጣ በወለደችበት በፖም ዛፍ ሥር ቀስቅሼ አስነሣሁህ።
6
በዘለዓለማዊ ፍቅር በልብህ ውስጥ እንደ ማኅተም አትመኝ፤ በክንድህም እንደ ማኅተም እኔን ብቻ ያዘኝ፤ ፍቅር እንደ ሞት የበረታች ናት፤ ቅናትም እንደ መቃብር የከፋች ናት፤ የእሳትዋ ወላፈን እንደ እግዚአብሔር ወላፈን ነው።
7
የውሃ ብዛት የፍቅርን እሳት ሊያጠፋ አይችልም፤ ጐርፍም ጠራርጎ ሊወስዳት አይችልም፤ ሰው ባለው ሀብት ሁሉ ፍቅርን ለመግዛት ቢሞክር ፍቅር በገንዘብ ስለማትገኝ ሰዎች ይዘባበቱበታል።
8
ገና ጡት ያላወጣች ትንሽ እኅት አለችን፤ ለጋብቻ ብትጠየቅ ለዚህች ለእኅታችን የምናደርግላት ምንድን ነው?
9
እርስዋ ቅጽር ብትሆን ኖሮ የብር ማማ እንሠራላት ነበር፤ እርስዋ የቅጽር በር ብትሆን ኖሮ ከሊባኖስ ዛፍ ሳንቃ የታነጸ መዝጊያ እንሠራላት ነበር።
10
እነሆ፥ እኔ ቅጽር ነኝ፤ ጡቶቼም እንደ ቅጽር ማማዎች ናቸው፤ ከውዴ ጋር ስሆን እርሱ ደስታንና ሰላምን ያገኛል።
11
ሰሎሞን በባዓልሃሞን የወይን ተክል ቦታ ነበረው፤ የወይኑንም ተክል ቦታ ለአትክልተኞች አከራየው፤ እያንዳንዳቸውም አንድ ሺህ ብር ያመጡለት ነበር፤
12
እኔ የግሌ የሆነ የወይን ተክል ቦታ አለኝ፤ ሰሎሞን ሆይ! አንተ አንድ ሺህ ብር፥ አትክልተኞቹ ሁለት መቶ ብር ልትወስዱ ትችላላችሁ።
13
አንቺ የእኔ ሙሽራ ሆይ! በአትክልት ቦታ ሆነሽ ጓደኞቼ ድምፅሽን ለመስማት ይፈልጋሉ፤ እስቲ ለእኔ ድምፅሽን አሰሚኝ።
14
ውዴ ሆይ! ፈጥነህ ወደ እኔ ና፤ የቅመም ተክሎች በሚበቅሉባቸው ተራራዎች ላይ የሚዘል አጋዘን ወይም የዋልያ ግልገል ምሰል።
← Chapter 7