bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
/
Song of Solomon 7
Song of Solomon 7
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
1
ልዕልት ሆይ! እግሮችሽ በነጠላ ጫማ ውስጥ ሲታዩ እንዴት ያምራሉ! ዳሌዎችሽ በብልኅ አንጥረኛ እጅ የተሠራ የዕንቊ ጌጥ ይመስላሉ፤
2
እንብርትሽ በወይን ጠጅ የተሞላ ብርሌ ይመስላል፤ ወገብሽ ዙሪያውን በውብ አበባ የታሰረ የስንዴ ነዶ ይመስላል።
3
ሁለቱ ጡቶችሽ መንታ የዋልያ ግልገሎችን ይመስላሉ።
4
አንገትሽ በዝሆን ጥርስ እንዳጌጠ ግንብ ነው፤ ዐይኖችሽ በታላቅዋ ከተማ በሐሴቦን የቅጽር በር አጠገብ የሚገኙ የውሃ ኲሬዎችን ይመስላሉ። አፍንጫሽ ወደ ደማስቆ አቅጣጫ ለመመልከት የተሠራውን የሊባኖስ ግንብ ይመስላል።
5
የራስሽ ቅርጽ እንደ ቀርሜሎስ ተራራ ነው፤ ዞማው ጠጒርሽም የሐር ጒንጒን የመሰለ ነው። ንጉሡም በሹሩባሽ ውበት ተማርኮአል።
6
ውዴ ሆይ! እንዴት ያማርሽ ነሽ? እንዴትስ ውብ ነሽ? ፍቅርሽ እንዴት ያስደስታል?
7
ቁመናሽ የዘንባባ ዛፍ ይመስላል፤ ጡቶችሽም ዘለላውን ይመስላሉ።
8
በዘንባባው ዛፍ ላይ ወጥቼ ፍሬውን መልቀም እወዳለሁ፤ ጡቶችሽ እንደ ወይን ዘለላ ዕቅፍ ይሁኑ፤ የእስትንፋስሽ መዓዛ እንደ ፖም ፍሬ ሽታ ነው።
9
የአፍሽም መዓዛ እንደ መልካም ወይን ጠጅ ነው። እንግዲያውስ መልካሙ የወይን ጠጅ በውዴ ከንፈሮችና ጥርሶች መካከል እየተንቆረቆረ በዝግታ ይውረድ።
10
እኔ የውዴ ነኝ፤ የእርሱም ምኞት ወደ እኔ ነው።
11
ውዴ ሆይ! ና፤ ከከተማ ወጥተን ወደ ገጠር እንሂድ፤ ሌሊቱን በዚያ እናሳልፍ።
12
ማልደንም ወደ ወይኑ ተክል ቦታ እንሂድ፤ የወይኑ አበባ ፈክቶ እንደ ሆነ፥ ሮማኑም አብቦ እንደ ሆነ እንይ፤ በዚያም ፍቅሬን እገልጥልሃለሁ።
13
የእንኰይ ፍሬ መዓዛና እንዲሁም ደስ የሚያሰኙ ልዩ ልዩ ፍራፍሬዎች ደጃችንን ሞልተውታል። ውዴ ሆይ! ከነዚህም ፍሬዎች የበሰሉትንና አዲስ የተቀጠፉትን ለአንተ አኑሬልሃለሁ።
← Chapter 6
Chapter 8 →