bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
/
Revelation 10
Revelation 10
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
1
ከዚህ በኋላ ደመና የለበሰ ሌላ ብርቱ መልአክ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ፤ በራሱ ዙሪያ ቀስተ ደመና ነበረ፤ ፊቱ እንደ ፀሐይ፥ እግሮቹ እንደ እሳት ዐምዶች ነበሩ፤
2
የተከፈተች ትንሽ የብራና ጥቅል መጽሐፍ በእጁ ይዞ ነበር፤ ቀኝ እግሩን በባሕር ላይ፥ ግራ እግሩንም በምድር ላይ አኖረ፤
3
የሚያገሣ የአንበሳን ድምፅ በመሰለ ታላቅ ድምፅም ጮኸ፤ በጮኸም ጊዜ ሰባቱ ነጐድጓዶች ድምፃቸውን አሰሙ።
4
ሰባቱ ነጐድጓዶች ድምፃቸውን ባሰሙ ጊዜ እኔ ልጽፍ አሰብኩ፤ ነገር ግን “ሰባቱ ነጐድጓዶች የተናገሩትን አሽገህ በምሥጢር ያዘው እንጂ አትጻፈው!” የሚል ድምፅ ከሰማይ ሰማሁ።
5
ከዚህ በኋላ በባሕርና በምድር ላይ ቆሞ ያየሁት መልአክ ቀኝ እጁን ወደ ሰማይ አነሣና
6
ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም በሚኖረው፥ ሰማይንና በእርሱ ውስጥ ያሉትን፥ ምድርንና በእርስዋ ውስጥ ያሉትን፥ ባሕርንና በእርሱም ውስጥ ያሉትን በፈጠረው አምላክ ስም ምሎ እንዲህ አለ፦ “ከእንግዲህ ወዲህ አይዘገይም!
7
ነገር ግን ሰባተኛው መልአክ እምቢልታውን በሚያሰማባቸው ቀኖች ለአገልጋዮቹ ለነቢያት ባስታወቃቸው መሠረት የእግዚአብሔር ምሥጢር ይፈጸማል።”
8
ከዚያ በኋላ ከሰማይ የሰማሁት ድምፅ “በባሕርና በምድር ላይ በቆመው መልአክ እጅ ላይ ያለውንና የተከፈተውን ጥቅል መጽሐፍ ሂድና ውሰድ” ሲል እንደገና ተናገረኝ።
9
ወደ መልአኩም ሄጄ “ትንሽቱን የብራና ጥቅል መጽሐፍ ስጠኝ” አልኩት፤ እርሱም “ውሰድና ብላት፤ በሆድህ መራራ ትሆናለች፤ በአፍህ ግን እንደ ማር. ትጣፍጣለች” አለኝ።
10
እኔም ትንሽቱን የብራና ጥቅል መጽሐፍ ከመልአኩ እጅ ወስጄ በላኋት፤ በአፌም እንደ ማር. ጣፈጠች፤ ከበላኋት በኋላ ግን ሆዴ መራራ ሆነ።
11
ከዚህ በኋላ “ስለ ብዙ ወገኖች፥ ሕዝቦች፥ ልዩ ልዩ ቋንቋ ስለሚናገሩ ሰዎችና ስለ ነገሥታት እንደ ገና ትንቢት መናገር አለብህ” ተብሎ ተነገረኝ።
← Chapter 9
Chapter 11 →