bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
/
Psalms 88
Psalms 88
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
1
አዳኜ እግዚአብሔር አምላክ ሆይ! ትረዳኝ ዘንድ በቀን ወደ አንተ እጮኻለሁ፤ ሌሊቱንም በአንተ ፊት አለቅሳለሁ።
2
እባክህ ጸሎቴን ስማ! ጩኸቴንም አድምጥ!
3
ብዙ መከራ ስለ ደረሰብኝ ለመሞት ተቃርቤአለሁ።
4
ሞተው ወደ መቃብር ከሚወርዱት ሰዎች ጋር ተቈጥሬአለሁ፤ ምንም ረዳት እንደሌለው ሰው ሆኜአለሁ።
5
በሙታን መካከል ፈጽሞ እንደ ተተዉ፥ ተገድለው በመቃብር እንደ ተጋደሙ፥ ከእንግዲህ ፈጽሞ እንደማታስታውሳቸውና የአንተ እንክብካቤ ከእነርሱ እንደ ተቋረጠ ሰዎች መስዬአለሁ።
6
አንተ ወደ መቃብር አዘቅት ወደ ጨለመውና ጥልቅ ወደ ሆነው ጒድጓድ አወረድከኝ።
7
ቊጣህ እጅግ ከብዶኛል፤ የቊጣህም ማዕበል አጥለቅልቆኛል።
8
ወዳጆቼ ሁሉ ከእኔ እንዲርቁ አደረግህ፤ በፊታቸውም አጸያፊ አደረግኸኝ፤ ዙሪያዬ ታጥሮአል፤ ማምለጫም የለኝም።
9
ሐዘኔ ከመብዛቱ የተነሣ ዐይኖቼ ደከሙ፤ እግዚአብሔር ሆይ! በየቀኑ ወደ አንተ እጮኻለሁ፤ እጆቼንም ለጸሎት ወደ አንተ እዘረጋለሁ።
10
ለሙታን ተአምራትን ታደርጋለህን? እነርሱስ ተነሥተው ያመሰግኑሃልን?
11
ዘለዓለማዊ ፍቅርህ በመቃብር፥ ታማኝነትህ በጥፋት ቦታ ይነገራልን?
12
ተአምራትህ በጨለማ ስፍራ ይታወቃሉን? ታዳጊነትህስ በተረሱ ሰዎች አገር ይታያልን?
13
እግዚአብሔር ሆይ! እንድትረዳኝ ወደ አንተ እጮኻለሁ፤ በየማለዳውም ወደ አንተ እጸልያለሁ።
14
እግዚአብሔር ሆይ! ለምን ትጥለኛለህ? ፊትህንስ ከእኔ ለምን ትሰውራለህ?
15
ከልጅነቴ ጀምሮ ጭንቀት ደርሶብኝ እስከ ሞት ተቃርቤአለሁ፤ ከማስደንገጥህ የተነሣ ተስፋ ቈርጬአለሁ።
16
ብርቱ ቊጣህ አደቀቀኝ፤ አስፈሪው ቅጣትህ ያጠፋኛል።
17
እነርሱ ቀኑን ሙሉ እንደ ጐርፍ ከበቡኝ፤ ፈጽመውም አሰጠሙኝ።
18
የቅርብ ወዳጆቼንና ጓደኞቼን ከእኔ አርቀህ ጨለማ ብቻ ከእኔ ጋር እንዲቀር አደረግህ።
← Chapter 87
Chapter 89 →