bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
/
Psalms 87
Psalms 87
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
1
እግዚአብሔር ከተማውን በተቀደሰው ተራራ ላይ መሠረተ።
2
እግዚአብሔር ከእስራኤል መኖሪያዎች ሁሉ ይልቅ የጽዮንን ደጆች ይወዳል።
3
አንቺ የእግዚአብሔር ከተማ ሆይ! አስደናቂ ነገሮች ስለ አንቺ ተነግረዋል።
4
ለእኔ በመታዘዝ የሚያገለግሉኝን ሕዝቦች በምመዘግብበት ጊዜ ግብጽንና ባቢሎንን እጨምራለሁ፤ ከኢየሩሳሌም ተወላጆች ጋር የፍልስጥኤምን፥ የጢሮስንና የኢትዮጵያን ሕዝቦች እጨምራለሁ።
5
ልዑል እግዚአብሔር ራሱ ስለሚመሠርታት ስለ ጽዮን፦ “ይህም ሕዝብ፥ ያም ሕዝብ በእርስዋ ውስጥ ተወልደዋል” ይባላል።
6
እግዚአብሔር ሕዝቦችን ሁሉ ይመዘግባል፤ እያንዳንዱንም “በጽዮን የተወለደ” ብሎ ይጠራዋል።
7
ዘማሪዎችና ጨፋሪዎች “የበረከታችን ሁሉ መገኛ ጽዮን ናት” እያሉ በደስታ ይዘምራሉ።
← Chapter 86
Chapter 88 →