bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
/
Psalms 8
Psalms 8
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
1
ጌታችንና እግዚአብሔር ሆይ! ስምህ በዓለም ሁሉ የገነነ ነው። ክብርህንም ከሰማያት ሁሉ በላይ አድርገሃል።
2
በጠላቶችህ ምክንያት ጠላትንና ተበቃይን ዝም ለማሰኘት ከልጆችና ጡት ከሚጠቡ አፍ፥ ምስጋናን አዘጋጀህ።
3
አንተ የፈጠርከውን ሰማይ በማይበት ጊዜ፥ በየስፍራቸው አጽንተህ ያኖርካቸውን ጨረቃንና ኮከቦችን በምመለከትበት ጊዜ፥
4
አንተ እርሱን ታስበው ዘንድ ሰው ምንድን ነው? እርሱንስ ትጐበኘው ዘንድ የሰው ልጅ ምንድን ነው?
5
ከመላእክት በጥቂቱ ብታሳንሰውም፥ የክብርና የምስጋና ዘውድ ጫንክለት፤
6
በፈጠርካቸው ፍጥረቶች ሁሉ ላይ፥ ገዢ አድርገህ ሾምከው፤ ከፍጥረትም ሁሉ በላይ አደረግኸው።
7
በጎችንና ከብቶችን፥ የዱር አራዊትንም፥
8
የሰማይ ወፎችንና የባሕር ዓሣዎችን፥ በባሕር ውስጥ ያሉ ፍጥረቶችን ሁሉ አስገዛህለት።
9
ጌታችን እግዚአብሔር ሆይ! ስምህ በዓለም ሁሉ የገነነ ነው!
← Chapter 7
Chapter 9 →