bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
/
Psalms 7
Psalms 7
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
1
እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ! የምተማመንብህ መማጸኛዬ አንተ ነህ፤ ከሚያሳድዱኝ ሁሉ ታደገኝ፤ አድነኝም።
2
ካላዳንከኝ ግን እንደ አንበሳ ነጥቀው ማንም ሊታደገኝ ወደማይችል ስፍራ ይወስዱኛል፤ ሰባብረውም ያደቁኛል።
3
እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ! አንድን ሰው እንኳ በድዬ ከሆነ፥ ለወዳጄ በመልካም ፈንታ ክፉ መልሼ ከሆነ፥ ጠላቴን ያለ ምክንያት እንዲሁ ጐድቼው ከሆነ፥ ከነዚህ ሁሉ ነገሮች አንዱን እንኳ አድርጌ ከሆነ፥
5
ጠላቴ አሳዶ ይያዘኝ! እስከ ሞት ድረስ ይርገጠኝ በአቧራም ላይ ጥሎ ክብር ያሳጣኝ!
6
እግዚአብሔር ሆይ! በቊጣህ ተነሥ፤ የጠላቶቼንም ቊጣ አስወግድ፤ ፍርድ እንዲስተካከል ባዘዝከው መሠረት እኔን ለመርዳት ተነሥ፤
7
ሕዝቦችን ሁሉ በዙሪያህ ሰብስብ፤ ከላይም ሆነህ ንገሥ።
8
እግዚአብሔር በሕዝቦች ላይ ይፈርዳል፤ ጌታ ሆይ! እንደ እውነተኛነቴና እንደ ታማኝነቴ ፍረድልኝ።
9
ኅሊናንና ልብን የምትመረምር ጻድቅ አምላክ ሆይ! የክፉዎችን ዐመፅ አጥፋ፤ የጻድቃንንም ደኅንነት ጠብቅ።
10
ልባቸው ቅን የሆኑትን የሚያድን፥ ልዑል እግዚአብሔር፥ እርሱ ጋሻዬ ነው።
11
እግዚአብሔር ሁልጊዜ በክፉዎች ላይ የሚፈርድ ትክክለኛ ዳኛ ነው።
12
ክፉዎች ከክፋታቸው የማይመለሱ ከሆነም፥ እግዚአብሔር ሰይፉን ይስላል፤ ቀስቱንም ያመቻቻል።
13
የሚገድሉ የጦር መሣሪያዎችን ያበጃል፤ እንደ እሳት የሚንበለበሉ ፍላጻዎችንም ያዘጋጃል።
14
ኃጢአተኞች በደልን ይፀንሳሉ፤ ተንኰልን ያረግዛሉ፤ ውሸትን ይወልዳሉ።
15
ለሌሎች ወጥመድ የሚሆን ጥልቅ ጒድጓድ ይቈፍራሉ፤ ነገር ግን በቈፈሩት ጒድጓድ ውስጥ እነርሱ ራሳቸው ይገቡበታል።
16
የሚያመጡት ችግር በራሳቸው ላይ ይደርሳል፤ በክፉ ድርጊታቸውም ዐናታቸው ይፈጠፈጣል።
17
ስለ እውነተኛነቱ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ፤ ለልዑል አምላክ ስም የምስጋና መዝሙር አቀርባለሁ።
← Chapter 6
Chapter 8 →