bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
/
Psalms 76
Psalms 76
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
1
እግዚአብሔር በይሁዳ የታወቀ ነው፤ ስሙም በእስራኤል ታላቅ ነው።
2
ቤቱን በሳሌም (ኢየሩሳሌም) አደረገ፤ በጽዮንም ተራራ ላይ ይኖራል።
3
በዚያም የሚያንጸባርቁ ፍላጻዎችን፥ ጋሻና ጦርን፥ ሌሎችንም የጦር መሣሪያዎች ሁሉ ሰባበረ።
4
አምላክ ሆይ አንተ አስፈሪ ነህ፤ ግርማህም ከታላላቅ ተራራዎች በላይ ነው።
5
ጀግኖች ወታደሮች የማረኩትን ተቀሙ፤ እጃቸውንም ማንሣት አቅቶአቸው የመጨረሻ እንቅልፍ አንቀላፉ
6
የያዕቆብ አምላክ ሆይ፥ አንተ በገሠጽካቸው ጊዜ ፈረሰኞች ከነፈረሶቻቸው ሞቱ።
7
እግዚአብሔር ሆይ አንተ ግን በሁሉ ዘንድ የተፈራህ ነህ፤ አንተ ስትቈጣ በፊትህ የሚቆም አንድ እንኳ አይኖርም፤
8
ፍርድህን ከሰማይ እንዲታወቅ ስታደርግ ምድሪቱ ፈርታ ጸጥ አለች፤
9
አንተ በምድር የተጨቈኑትን ሁሉ ለመቤዠት፥ ለፍርድ በተነሣህ ጊዜ ዓለም ጸጥ አለ።
10
የሰው ቊጣ አንተን ያመሰግንሃል፤ ከጦርነት የተረፉትም በዓልህን ያከብራሉ።
11
መፈራት ለሚገባው ለእግዚአብሔር ለአምላካችሁ ተስላችሁ የተሳላችሁትን ስእለት ፈጽሙ፤ እናንተ በቅርብ ያላችሁ ሕዝቦች መባ አምጡለት።
12
ትዕቢተኞች የሆኑትን መሳፍንት ያዋርዳል፤ ታላላቅ ነገሥታትንም ያርበደብዳል።
← Chapter 75
Chapter 77 →