bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
/
Psalms 75
Psalms 75
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
1
አምላክ ሆይ፥ እናመሰግንሃለን፤ አንተ ወደ እኛ ስለ ቀረብክ ለስምህ ምስጋና እናቀርባለን፤ ስላደረግኸው ድንቅ ሥራ እንናገራለን።
2
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ፍርድ የምሰጥበትን ጊዜ ወስኛለሁ፤ በዚያን ጊዜ በትክክል እፈርዳለሁ።
3
ምድር ስትናወጥ፥ በውስጥዋ ያሉትም ሕያዋን ፍጥረቶች ቢንቀጠቀጡም እንኳ እኔ የምድርን መሠረት አጸናለሁ።
4
ትዕቢተኞችን ‘አትታበዩ’ ክፉዎችን ‘አታምፁ’ እላቸዋለሁ፤
5
በእግዚአብሔር ላይ ራስህን ከፍ ከፍ አታድርግ፤ ወይም በትዕቢት አትናገር።”
6
ፍርድ ከምሥራቅ ወይም ከምዕራብ፥ ወይም ከምድረ በዳ አይመጣም፤
7
በአንዱ ላይ የሚፈርድ፥ ሌላውን ነጻ የሚያወጣ፥ ትክክለኛ ፈራጅ እግዚአብሔር ነው።
8
እግዚአብሔር የተቀመመ ወይን ጠጅ የተሞላበትን ጽዋ በእጁ ይዞአል፤ በቊጣው ሲያፈስሰው ክፉዎች ሁሉ ይጠጡታል፤ እስከ መጨረሻው ጠብታ ድረስ ይጨልጡታል።
9
እኔ ግን ስለ ያዕቆብ አምላክ ከመናገር ስለ ክብሩም ከመዘመር ከቶ አልቈጠብም።
10
እርሱ የክፉዎችን ኀይል ይሰብራል፤ የጻድቃን ኀይል ግን እየጨመረ ይሄዳል።
← Chapter 74
Chapter 76 →