bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
/
Psalms 67
Psalms 67
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
1
እግዚአብሔር ይማረን፥ ይባርከንም፤ የፊቱ ብርሃን በላያችን ይብራ።
2
ዓለም በሙሉ የአንተን መንገድ፥ ሕዝቦችም የአንተን አዳኝነት ይወቁ።
3
አምላክ ሆይ፥ ሕዝቦች ያመስግኑህ፤ ሕዝቦች ሁሉ ያመስግኑህ።
4
ለሕዝቦች በቅንነት ስለምትፈርድና የዓለምን መንግሥታት ሁሉ ስለምትመራ፤ መንግሥታት ደስ ይበላቸው፤ በሐሤትም እልል ይበሉ።
5
አምላክ ሆይ! ሕዝቦች ያመስግኑህ፤ ሕዝቦች ሁሉ ያመስግኑህ።
6
በዚያን ጊዜ ምድር ፍሬ ትሰጣለች፤ እግዚአብሔር አምላካችን ይባርከናል።
7
እግዚአብሔር ስለሚባርከንም በምድር ዳርቻ ያሉ ሁሉ ይፈሩታል።
← Chapter 66
Chapter 68 →