bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
/
Psalms 66
Psalms 66
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
1
ሕዝቦች ሁሉ ድምፃችሁን ከፍ አድርጋችሁ፥ በእልልታ እግዚአብሔርን አመስግኑ!
2
ስሙን በማክበር ዘምሩ፤ በምስጋናም አክብሩት።
3
እንዲህም በሉት፤ “ሥራህ እንዴት ድንቅ ነው! ኀይልህ እጅግ ታላቅ በመሆኑ ጠላቶችህ በፍርሃት በፊትህ ይሸማቀቃሉ።
4
በምድር ያሉ ሁሉ ይሰግዱልሃል፤ የምስጋናም መዝሙር ያቀርቡልሃል፤ ስምህንም በማክበር ይዘምራሉ።”
5
እግዚአብሔር ያደረገውን ሁሉ ኑ እዩ፤ እርሱ ለሰው ልጆች ድንቅ ሥራ ሠርቶአል።
6
እርሱ ባሕሩን ወደ ደረቅ መሬት ለውጦአል፤ የቀድሞ አባቶቻችን ወንዙን በእግር ተሻግረዋል፤ እኛም እርሱ ባደረገው ነገር ደስ ብሎናል።
7
በኀይሉ ለዘለዓለም ይገዛል፤ በዐይኑም መንግሥታትን አተኲሮ ያያል፤ ስለዚህ ዐመፀኞች በእርሱ ላይ ባይነሡ ይሻላቸዋል።
8
አሕዛብ ሁሉ አምላካችንን አክብሩ፤ ድምፃችሁንም ከፍ አድርጋችሁ ለእርሱ ምስጋና አቅርቡ።
9
እርሱ በሕይወት ጠብቆናል፤ እንድንወድቅም አላደረገም።
10
አምላክ ሆይ! ብር በእሳት ተፈትኖ እንደሚጠራ ፈተንከን።
11
በወጥመድ አጠመድከን፤ ከባድ ሸክምንም ጫንክብን።
12
ጠላቶቻችን በግፍ እንዲረግጡን አደረግህ፤ በእሳትና በጐርፍ መካከል አለፍን፤ አሁን ግን ብልጽግና ወደ መላበት ወደ ሰፊ ቦታ አመጣኸን።
13
የሚቃጠል መሥዋዕት ይዤ ወደ ቤትህ እገባለሁ፤ ስእለቴንም አቀርብልሃለሁ።
14
መከራ በደረሰብኝ ጊዜ “ለአንተ እሰጣለሁ” ያልኩትን ስእለት አቀርብልሃለሁ።
15
የሰቡ እንስሶችን የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጌ እንዲሁም መዓዛው ደስ የሚያሰኝ የአውራ በግ መሥዋዕት አቀርብልሃለሁ፤ ኰርማዎችንና ፍየሎችንም አዘጋጅልሃለሁ።
16
እግዚአብሔር ያደረገልኝን ሁሉ እንድነግራችሁ፥ እግዚአብሔርን የምትፈሩ ሁሉ ኑ ስሙ።
17
ድምፄን ከፍ አድርጌ ወደ እርሱ ጸለይኩ፤ በአንደበቴም አመሰገንኩት።
18
ኃጢአቴን ሳልናዘዝ በልቤ ሰውሬ ቢሆን ኖሮ፥ እግዚአብሔር ጸሎቴን ባልሰማም ነበር።
19
አሁን ግን በእርግጥ እግዚአብሔር ሰምቶኛል፤ የልመናዬንም ድምፅ አድምጦአል።
20
ጸሎቴን ለሰማና ዘለዓለማዊ ፍቅሩን ላልነሣኝ አምላክ ምስጋና ይድረሰው።
← Chapter 65
Chapter 67 →