bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
/
Psalms 142
Psalms 142
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
1
ድምፄን ከፍ አድርጌ ወደ እግዚአብሔር እጮኻለሁ፤ ምሕረት እንዲያደርግልኝ እለምነዋለሁ።
2
አቤቱታዬን ሁሉ በፊቱ አቀርባለሁ፤ ችግሬንም ሁሉ እነግረዋለሁ።
3
ተስፋ ለመቊረጥ ጥቂት በቀረኝ ጊዜ ምን ማድረግ እንደሚገባኝ ያውቃል፤ ጠላቶቼ በምሄድበት መንገድ ላይ ወጥመድ ዘረጉብኝ።
4
በዙሪያዬ ስመለከት መሸሸጊያ የሚሆነኝ አጣሁ፤ አንድም እንኳ የሚረዳኝ ሰው አልነበረም፤ የሚጠብቀኝና የሚጠነቀቅልኝም አልነበረም።
5
እግዚአብሔር ሆይ! እንድትረዳኝ ወደ አንተ እጮኻለሁ፤ እግዚአብሔር ሆይ! ጠባቂዬ አንተ ነህ፤ በሕያዋን ምድር ዕድል ፈንታዬ አንተ ነህ።
6
በጣም ተስፋ የቈረጥሁ ስለ ሆነ እንድትረዳኝ ወደ አንተ ስጮኽ ስማኝ፤ እጅግ በርትተውብኛልና ከጠላቶቼ አድነኝ።
7
አመሰግንህ ዘንድ ከእስራቴ አውጣኝ፤ ለእኔ ያደረግኸውን ያንተን የቸርነት ሥራ በሚያዩበት ጊዜ ሕዝብህ በዙሪያዬ ይሰበሰባሉ።
← Chapter 141
Chapter 143 →