bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
/
Psalms 141
Psalms 141
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
1
እግዚአብሔር ሆይ! ወደ አንተ እጣራለሁ፤ በፍጥነትም እርዳኝ! ወደ አንተም ስጮኽ ስማኝ!
2
ጸሎቴን እንደ ዕጣን፥ የተዘረጉትን እጆቼን እንደ ማታ መሥዋዕት አድርገህ ተቀበል።
3
እግዚአብሔር ሆይ! ለአፌ ጠባቂ አኑር፤ በከንፈሮቼም በር ላይ ዘበኛ አቁም።
4
ስሕተት ለማድረግ ከመመኘትና ከክፉ አድራጊዎች ጋር በክፉ ሥራ ከመተባበር ጠብቀኝ፤ የበዓላቸው ግብዣ ተካፋይ ከመሆን ጠብቀኝ።
5
ደግ ሰው በቅንነት መንፈስ ሊቀጣኝና ሊገሥጸኝ ይችላል፤ ከክፉ ሰዎች ግን ክብርን እንኳ አልቀበልም፤ ዘወትርም ክፉ ሥራቸውን በመቃወም እጸልያለሁ።
6
ዳኞቻቸው በገደል አለት ላይ በተጣሉ ጊዜ ሕዝቦቻቸው የእኔ ቃል እውነት መሆኑን ያረጋግጣሉ።
7
መሬት እንደሚታረስና ጓሉ እንደሚፈራርስ የእነርሱም አጥንቶች በመቃብር አፍ ላይ ይበታተናሉ።
8
እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ! እኔ ግን በአንተ መተማመኔን አልተውም፤ የአንተንም ጥበቃ ስለምፈልግ እንድሞት አታድርገኝ!
9
ከዘረጉብኝ ወጥመድ ጠብቀኝ፤ ከክፉ አድራጊዎችም መሰናክል አድነኝ።
10
እኔ ያለ ጒዳት ሳልፍ ክፉዎች ባጠመዱት ወጥመድ ይያዙ።
← Chapter 140
Chapter 142 →