bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
/
Isaiah 15
Isaiah 15
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
1
ስለ ሞአብም የተነገረው ቃል ይህ ነው፤ የዔርና ቂር ከተሞች በአንድ ቀን ሌሊት ተደመሰሱ፥ የሞአብ ምድር ጭር አለች፤
2
የጺቦን ሕዝብም በቤተ ጣዖታቸው ለማልቀስ ወደ ኰረብታ ይወጣሉ፤ የሞአብ ሕዝብ ስለ ነቦና ስለ ሜዳባ ከተሞቻቸው በከባድ ሐዘን ያለቅሳሉ፤ ከሐዘናቸውም የተነሣ ጠጒራቸውንና ጢማቸውን ተላጭተዋል።
3
በየመንገዱ የሚታዩት ማቅ ለብሰው ነው፤ በሰገነቶቻቸውና በአደባባዮቻቸው ሁሉም እንባቸውን እያፈሰሱ ያለቅሳሉ።
4
የሐሴቦንና የኤልዓሌ ሕዝቦች ይጮኻሉ፤ የጩኸታቸውም ድምፅ እስከ ያሐጽ ድረስ ይሰማል፥ የሞአብ ወታደሮች ሳይቀሩ ወኔያቸው ከድቶአቸው በፍርሃት ተርበደበዱ።
5
ስለ ሞአብ ከልቤ አለቅሳለሁ፤ ሕዝቡ ወደ ጾዓርና ወደ ዔግላት ሸሊሺያ ኰበለሉ፤ ጥቂቶችም ወደ ሉሒት አቀበት ወጡ፤ በሚወጡበትም ጊዜ ያለቅሱ ነበር፤ ሌሎች ደግሞ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ስለ ጥፋታቸው እያለቀሱ ወደ ሖሮናይም ለማምለጥ ይሞክራሉ።
6
የኒምሪም ወንዞች ደርቀዋል፤ ምንም ልምላሜ ሳይቀር በአጠገቡ ያለው ሣር ደርቆአል።
7
ሕዝቡ የሰበሰቡትን ሀብት እንደ ያዙ የአኻያ ዛፍ የበቀለበትን ሸለቆ ተሻግረው ይሄዳሉ፤
8
በሞአብ ጠረፎች በየስፍራው ጩኸት ይሰማል፤ ጩኸቱም እስከ ኤግላይምና እስከ ብኤርኤሊም ደርሶአል።
9
በዲቦን ከተማ የሚገኘው ወንዝ በደም የተሞላ ነው፤ ሆኖም በዲቦን ላይ እግዚአብሔር ከዚያ የባሰ ነገር ያመጣል፤ ከሞአብ ሸሽተው የሚያመልጡትንና እዚያም ከሞት የተረፉትን ሁሉ አንበሳ ልኮ ያጠፋቸዋል።
← Chapter 14
Chapter 16 →