bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
/
Isaiah 14
Isaiah 14
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
1
እግዚአብሔር ለሕዝቡ ለእስራኤል እንደገና ምሕረትን ያደርጋል፤ የራሱ ወገኖችም አድርጎ ይመርጣቸዋል፤ እንደገናም በአገራቸው እንዲኖሩ ይፈቅድላቸዋል፤ መጻተኞችም እንኳ መጥተው ከእነርሱ ጋር ተስማምተው አብረው ይኖራሉ።
2
የብዙ አሕዛብ መንግሥታት የእስራኤል ሕዝብ እግዚአብሔር ወደ ሰጣቸው አገር እንዲመለሱ ይረዱአቸዋል፤ አሕዛብ እንደ ባሪያዎች ሆነው የእስራኤልን ሕዝብ ያገለግላሉ፤ ቀድሞ እስራኤልን ማርከው የነበሩ አሁን ደግሞ በእስራኤል እጅ ይማረካሉ፤ ስለዚህም የእስራኤል ሕዝብ ቀድሞ ይጨቊኑአቸው የነበሩትን ሁሉ የመግዛት ሥልጣን ይኖራቸዋል።
3
እግዚአብሔር በጭንቀትና በሥቃይ ከምትኖሩበት ከባርነት ኑሮ ነጻ በሚያወጣችሁ ጊዜ
4
በባቢሎን ንጉሥ ላይ እንዲህ እያላችሁ ታፌዙበታላችሁ፦ “እነሆ ጨቋኙ ንጉሥ ወደቀ! ከእንግዲህ ወዲህ ማንንም አይጨቊንም!
5
እግዚአብሔር የክፉ ገዢዎችን ኀይልና ሥልጣን አስወግዶአል፤
6
እነዚህ ገዢዎች በቊጣቸው ሕዝቦችን ሲጨቊኑ ኖረዋል፤ ያሸነፉአቸውንም ያለማቋረጥ ሲያሠቃዩአቸው ነበር፤
7
በመጨረሻ ግን እነሆ ዓለም ሁሉ የሰላም ዕረፍት ያገኛል፤ ሁሉም በደስታ ይዘምራሉ።
8
የሊባኖስ ዛፎችና ዝግባዎች እንኳ ስለ ወደቀው ንጉሥ ደስታቸውን ይገልጣሉ፤ እርሱ ስለ ተወገደ ከእንግዲህ ወዲህ በእነርሱ ላይ መጥረቢያ የሚያነሣባቸው ሰው አይኖርም።
9
“የሙታን ዓለም የባቢሎንን ንጉሥ ለመቀበል ተዘጋጅታለች፤ የሙታን መናፍስትም ሁሉ እርሱን ለመቀበል ይንቀሳቀሳሉ፤ በምድር ላይ ኀያላን የነበሩ እጅ ይነሡታል፤ ነገሥታት የነበሩትም ከዙፋናቸው ይነሡለታል።
10
እንዲህም ይሉታል፥ ‘አንተም ደግሞ እንደኛ ደካማ ሆንክ! ከእኛም እንደ አንዱ ሆንክ
11
ቀድሞ ስለ ክብርህ በመሰንቆ ይዘመርልህ የነበረው ቆመ፤ አሁን አንተ በትዕቢትህ ወደ ሙታን ዓለም ወረድክ። ስለዚህ አልጋህ ምስጥ፥ ልብስህም የትል መንጋ ሆኖአል።’ ”
12
አንተ በሚያበራው የአጥቢያ ኮከብ የተመሰልክ የባቢሎን ንጉሥ ሆይ! እንደ ሰማይ ከፍ ካለው ክብርህ እንዴት ወደቅኽ! መንግሥታትን ሁሉ ታዋርድ ነበር፤ አሁን ግን ወደ መሬት ተጣልክ።
13
አንተ እንዲህ ብለህ አስበህ ነበር፦ “ወደ ሰማይ ወጥቼ ከእግዚአብሔር ከዋክብት በላይ ዙፋኔን እዘረጋለሁ፤ በስተሰሜን ዳርቻ አማልክት በሚሰበሰቡበት ቦታ በተራራ ላይ እቀመጣለሁ።
14
ከደመናዎችም በላይ ወጥቼ በልዑል አምላክ እመሰላለሁ” ብለህ አስበህ ነበር።
15
ነገር ግን ወደ ሙታን ዓለም፥ ወደ ጥልቁ ጒድጓድ ወርደሃል።
16
ሙታንም የአንተን ሁኔታ አይተው በመገረም ተመልክተው እንዲህ ይላሉ፦ “ያ ዓለምን ያንቀጠቀጠና መንግሥታትን ያናወጠ ሰው ይህ ነውን?
17
ከተሞችን ደምስሶ ዓለምን ወደ ምድረ በዳነት የለወጣት ሰው ይህ ነውን? እስረኞች ነጻ እንዳይለቀቁና ወደ ቤታቸው እንዳይገቡ የሚያደርግ እርሱ አልነበረምን?”
18
ነገሥታት ሲሞቱ በክብር ይቀበራሉ።
19
አንተ ግን ሳትቀበር በእግር እንደሚረጋገጥ የዛፍ ቅጠል የተጣልክ ሆነሃል፤ ሬሳህም በጦርነት ላይ በሞቱ ሰዎች ሬሳ ተሸፍኖአል፤ ከእነርሱም ሬሳ ጋር በድንጋያማ ጒድጓድ ውስጥ ተጥሎ ተረግጦአል።
20
አንተ አገርህን አጥፍተህ፥ የገዛ ሕዝብህን ፈጅተሃል፤ ስለዚህም አንተ እንደ ሌሎች መንግሥታት መቃብር የማግኘት ዕድል አይኖርህም፤ ከክፉ ቤተሰብ መካከል የሚተርፍ ዘር አይኖርም።
21
እንግዲህ የልጆቹ መታረድ አሁኑኑ ይዘጋጅ፤ የዚህ ንጉሥ ልጆች በቀድሞ አባቶቻቸው ኃጢአት የሞት ፍርድ ይጠብቃቸዋል፤ ከእንግዲህ ወዲህ ከእነርሱ ማንም ምድርን መውረስም ሆነ ከተሞችን መሥራት አይችልም።
22
የሠራዊት አምላክ እንዲህ ይላል “በባቢሎን ላይ አደጋ ጥዬ አፈራርሳታለሁ፤ ምንም ነገር አላስቀርላትም፤ ለዘር እንኳ የሚተርፍ ትውልድ አይኖራትም፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።
23
ባቢሎንን ረግረግ ስለማደርጋት የአልቅት መፈልፈያ ትሆናለች፤ ባቢሎንን ሁሉን ነገር ጠራርጎ በሚወስድ መጥረጊያ እጠርጋታለሁ፤ እኔ የሠራዊት አምላክ ይህን ተናግሬአለሁ።”
24
የሠራዊት አምላክ እንዲህ ሲል ምሎአል፥ “ያቀድኩት ነገር ሁሉ ተፈጻሚ ይሆናል፤ የወሰንኩትም ነገር ሥራ ላይ ይውላል።
25
አሦራውያንን ለእስራኤል በሰጠኋት ምድሬ ላይ እደመስሳቸዋለሁ፤ በተራሮቼም ላይ እረግጣቸዋለሁ፤ ሕዝቤንም ከአሦራውያን የአገዛዝ ቀንበርና ከነበረባቸውም ከባድ ሸክም ነጻ አወጣቸዋለሁ።
26
መላውን ዓለም በሚመለከት ያለኝም ዕቅድ ይህ ነው፤ መንግሥታትን ለመቅጣት ክንዴን ዘርግቼአለሁ።”
27
የሠራዊት አምላክ ይህን ሁሉ ለማድረግ ወስኖአል፤ ይህ እንዳይሆን የሚያደርግ ማነው? ለመቅጣትም ክንዱን ዘርግቶአል፤ ተከላክሎ ሊያቆመው የሚችልስ ማን ነው?
28
ንጉሥ አካዝ በሞተበት ዓመት የተነገረው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው፤
29
የፍልስጥኤም ሕዝብ ሆይ! እነሆ የተደበደባችሁበት በትር ተሰበረ፤ ሆኖም ደስ ሊላችሁ አይገባም፤ አንድ እባብ በሞተ ጊዜ ሌላ ከእርሱ የባሰ በቦታው ይተካል፤ ከእባብ ዕንቊላል በክንፍ የሚበር እሳት የመሰለ ዘንዶ ይፈለፈላል።
30
እጅግ የደኸዩ መጠጊያ ያገኛሉ፤ ድኽነት ያጠቃቸውም ተዝናንተው ይኖራሉ፤ የእናንተን ልጆች ግን በራብ እገድላለሁ፤ የተረፋችሁትንም አጠፋለሁ።
31
በመግቢያው በር ሆናችሁ ወዮ በሉ! በከተማው ውስጥ ሆናችሁ ኡኡ! በሉ፤ ከወታደሮቹ አንዱ እንኳ ወደ ኋላ የማይል ኀይለኛ ጠላት ከሰሜን ስለ መጣ ፍልስጥኤማውያን ሁሉ በፍርሃት ይርበድበዱ!
32
ከፍልስጥኤም ለሚመጡ መልእክተኞች የምንሰጠው መልስ ምንድን ነው? እግዚአብሔር ጽዮንን እንደገና መመሥረቱንና በሥቃይ ይኖሩ የነበሩ ሕዝቡ መጠጊያ አግኝተው በሰላም እንዲኖሩ ማድረጉን እንነግራቸዋለን።
← Chapter 13
Chapter 15 →