bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Psalms 95
Psalms 95
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
ኑ፤ ደስ እያለን ለእግዚአብሔር እንዘምር፤ በድነታችንም ዐለት እልል እንበል።
2
ምስጋና ይዘን ፊቱ እንቅረብ፤ በዝማሬም እናወድሰው።
3
እግዚአብሔር ታላቅ አምላክ ነውና፤ ከአማልክትም ሁሉ በላይ ታላቅ ንጉሥ ነው።
4
የምድር ጥልቆች በእጁ ናቸው፤ የተራራ ጫፎችም የእርሱ ናቸው።
5
እርሱ ፈጥሯታልና ባሕር የእርሱ ናት፤ እጁም የብስን አበጀ።
6
ኑ፤ እናምልከው፤ እንስገድለትም፤ በፈጣሪያችን በእግዚአብሔር ፊት እንንበርከክ፤
7
እርሱ አምላካችን ነውና፤ እኛም በእጁ ጥበቃ ሥር ያለን በጎቹ፣ የመሰማሪያውም ሕዝብ ነን። ዛሬ ድምፁን ብትሰሙ፣
8
በምድረ በዳ በነበራችሁበት ቀን በማሳህ፣ በመሪባም እንዳደረጋችሁት፣ ልባችሁን አታደንድኑ።
9
ሥራዬን ቢያዩም፣ አባቶቻችሁ በዚያ ፈተኑኝ፤ ተፈታተኑኝም።
10
ያን ትውልድ አርባ ዓመት ሙሉ ተቈጣሁት፤ እኔም፣ “ልቡ የሸፈተ ሕዝብ ነው፤ መንገዴንም አላወቀም” አልሁ።
11
ስለዚህ፣ “ፈጽሞ ወደ ዕረፍቴ አይገቡም” ብዬ፣ በቍጣዬ ማልሁ።
← Chapter 94
Chapter 96 →