bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Psalms 66
Psalms 66
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
ምድር ሁሉ ለእግዚአብሔር እልል ይበል!
2
ለስሙ ክብር ዘምሩ፤ ውዳሴውንም አድምቁ
3
እግዚአብሔርን እንዲህ በሉት፤ “ሥራህ እንዴት ግሩም ነው! ጠላቶችህ ከኀይልህ ታላቅነት የተነሣ፣ በፊትህ ይርዳሉ።
4
ምድር ሁሉ ይሰግድልሃል፤ በዝማሬ ያመሰግኑሃል፤ ለስምህም ይዘምራሉ።”
5
ኑና፣ እግዚአብሔር ያደረገውን እዩ፤ በሰዎች መካከል ሥራው አስፈሪ ነው!
6
ባሕሩን የብስ አደረገው፤ ወንዙን በእግር ተሻገሩ፤ ኑ፣ በእርሱ ደስ ይበለን።
7
በኀይሉ ለዘላለም ይገዛል፤ ዐይኖቹ ሕዝቦችን ይመለከታሉ፤ እንግዲህ ዐመፀኞች ቀና ቀና አይበሉ።
8
ሕዝቦች ሆይ፤ አምላካችንን ባርኩ፤ የምስጋናውንም ድምፅ አሰሙ።
9
እኛን በሕይወት የሚያኖረን፣ እግራችንንም ከመንሸራተት የሚጠብቅ እርሱ ነው።
10
አምላክ ሆይ፤ አንተ ፈተንኸን፤ እንደ ብርም አነጠርኸን።
11
ወደ ወጥመድ አገባኸን፤ በጀርባችንም ሸክም ጫንህብን።
12
ሰዎች በራሳችን ላይ እንዲፈነጩ አደረግህ፤ በእሳትና በውሃ መካከል ዐለፍን፤ የኋላ ኋላ ግን ወደ በረከት አመጣኸን።
13
የሚቃጠል መሥዋዕት ይዤ ወደ መቅደስህ እገባለሁ፤ ስእለቴንም ለአንተ እፈጽማለሁ፤
14
በመከራ ጊዜ ከአፌ የወጣ፣ በከንፈሬም የተናገርሁት ስእለት ነው።
15
ፍሪዳዎችን የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጌ፣ አውራ በጎችንም የሚጤስ ቍርባን አድርጌ አቀርብልሃለሁ፤ ኰርማዎችንና ፍየሎችንም እሠዋልሃለሁ።
16
እግዚአብሔርን የምትፈሩ ሁሉ፤ ኑና ስሙ፤ ለነፍሴ ያደረገላትን ልንገራችሁ።
17
በአፌ ወደ እርሱ ጮኽሁ፤ በአንደበቴም አመሰገንሁት።
18
ኀጢአትን በልቤ አስተናግጄ ቢሆን ኖሮ፣ ጌታ ባልሰማኝ ነበር።
19
አሁን ግን እግዚአብሔር በርግጥ ሰምቶኛል፤ ጸሎቴንም አድምጧል።
20
ጸሎቴን ያልናቀ፣ ምሕረቱንም ከእኔ ያላራቀ፣ እግዚአብሔር ምስጋና ይድረሰው።
← Chapter 65
Chapter 67 →