bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Psalms 65
Psalms 65
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
እግዚአብሔር ሆይ፤ በጽዮን ለአንተ ውዳሴ ይገባል፤ ለአንተ የተሳልነውን እንፈጽማለን።
2
ጸሎትን የምትሰማ ሆይ፤ የሰው ልጆች ሁሉ ወደ አንተ ይመጣሉ።
3
ኀጢአት ባጥለቀለቀን ጊዜ፣ አንተ መተላለፋችንን ይቅር አልህ።
4
አንተ የመረጥኸው፣ ወደ ራስህ ያቀረብኸው፣ በአደባባይህም ያኖርኸው ምስጉን ነው! ከተቀደሰው መቅደስህ፣ ከቤትህም በረከት እንረካለን።
5
እግዚአብሔር አዳኛችን ሆይ፤ በጽድቅ ድንቅ አሠራር መልስልን፤ አንተ ለምድር ዳርቻ ሁሉ፣ በርቀት ላለውም ባሕር ተስፋ ነህ።
6
ተራሮችን በብርታትህ መሠረትህ፤ ኀይልንም ታጥቀሃል።
7
አንተ የባሕሮችን ማስገምገም፣ የማዕበላቸውን ፉጨት፣ የሕዝቦችንም ሁከት ጸጥ ታደርጋለህ።
8
ርቀው በምድር ዳርቻ ያሉት ከድንቅ ሥራህ የተነሣ ይደነግጣሉ፤ የንጋትንና የምሽትን መምጫዎች፣ በደስታ እልል እንዲሉ ታደርጋቸዋለህ።
9
ምድርን ትጐበኛለህ፤ ታጠጣለህም፤ እጅግ ታበለጥጋታለህም። ለሰዎች እህልን ይለግሱ ዘንድ፣ የእግዚአብሔር ወንዞች ውሃን የተሞሉ ናቸው፤ አንተ እንዲህ እንዲሆን ወስነሃልና።
10
ትልሟን በውሃ ታረሰርሳለህ፤ ቦይዋን ታስተካክላለህ፤ በካፊያ ታለሰልሳለህ፤ ቡቃያዋንም ትባርካለህ።
11
ለዘመኑ በጎነትህን ታጐናጽፈዋለህ፤ ሠረገላህም በረከትን ተሞልቶ ይፈስሳል።
12
የምድረ በዳው ሣር እጅግ ለመለመ፤ ኰረብቶችም ደስታን ተጐናጸፉ።
13
ሜዳዎች መንጋ በመንጋ ሆኑ፤ ሸለቆችም በእህል ተሸፈኑ፤ እልል ይላሉ፤ ይዘምራሉም።
← Chapter 64
Chapter 66 →