bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Psalms 60
Psalms 60
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
እግዚአብሔር ሆይ፤ ጣልኸን፤ አንኰታኰትኸን፤ ተቈጣኸንም፤ አሁን ግን መልሰህ አብጀን።
2
ምድሪቱን አናወጥሃት፤ ፍርክስክስ አደረግሃት፤ ትንገዳገዳለችና ስብራቷን ጠግን።
3
ለሕዝብህ አበሳውን አሳየኸው፤ ናላ የሚያዞር የወይን ጠጅ እንድንጠጣም ሰጠኸን።
4
ነገር ግን ከቀስት እንዲያመልጡ፣ ለሚፈሩህ ምልክት አቆምህላቸው።
5
ወዳጆችህ ይድኑ ዘንድ፣ በቀኝ እጅህ ርዳን፤ መልስም ስጠን።
6
እግዚአብሔር ከመቅደሱ እንዲህ ሲል ተናገረ፤ “ደስ እያለኝ የሴኬምን ምድር እሸነሽናለሁ፤ የሱኮትን ሸለቆ አከፋፍላለሁ።
7
ገለዓድ የእኔ ነው፤ ምናሴም የእኔ ነው፤ ኤፍሬም የራስ ቍሬ ነው፤ ይሁዳም በትረ መንግሥቴ ነው።
8
ሞዓብ የመታጠቢያ ገንዳዬ ነው፤ በኤዶምያስ ላይ ጫማዬን እወረውራለሁ፤ በፍልስጥኤም ላይ በድል እልል እላለሁ።”
9
ወደ ተመሸገው ከተማ ማን ያመጣኛል? ማንስ ወደ ኤዶምያስ ይመራኛል?
10
አምላክ ሆይ፤ የጣልኸን አንተ አይደለህምን? እግዚአብሔር ሆይ፤ ከሰራዊታችን ጋር እኮ አልወጣ አልህ!
11
በጠላት ላይ ድልን አቀዳጀን፤ የሰው ርዳታ ከንቱ ነውና።
12
በእግዚአብሔር ክንደ ብርቱ እንሆናለን፤ ጠላቶቻችንን የሚረጋግጥልን እርሱ ነውና።
← Chapter 59
Chapter 61 →