bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Psalms 59
Psalms 59
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
አምላክ ሆይ፤ ከጠላቶቼ እጅ አድነኝ፤ ሊያጠቁኝ ከሚነሡብኝም ጠብቀኝ።
2
ከክፉ አድራጊዎች ታደገኝ፤ ደም ከተጠሙ ሰዎችም አድነኝ።
3
እነሆ በነፍሴ ላይ አድብተዋልና፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ ጨካኞች ያለ በደሌ፣ ያለ ኀጢአቴ በላዬ ተሰብስበው ዶለቱብኝ።
4
እነርሱ ያለ በደሌ ሊያጠቁኝ ተዘጋጅተው መጡ፤ አንተ ግን ትረዳኝ ዘንድ ተነሥ፤ ሁኔታዬንም ተመልከት።
5
የሰራዊት አምላክ የሆንህ፣ አንተ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤ ሕዝቦችን ሁሉ ለመቅጣት ተነሥ፤ በተንኰላቸው በደል የሚፈጽሙትንም ሁሉ አትማራቸው።
6
እንደ ውሻ እያላዘኑ፣ በምሽት ተመልሰው ይመጣሉ፤ በከተማዪቱም ዙሪያ ይራወጣሉ።
7
ከአፋቸው የሚወጣውን ተመልከት፤ ሰይፍ በከንፈራቸው ላይ አለ፤ “ማን ሊሰማን ይችላል?” ይላሉና።
8
እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ግን ትሥቅባቸዋለህ፤ ሕዝቦችን ሁሉ በንቀት ታያቸዋለህ።
9
ብርታቴ ሆይ፤ አንተን እጠብቃለሁ፤ አምላክ ሆይ፤ አንተ መጠጊያዬ ነህና።
10
እግዚአብሔር በምሕረቱ ይገናኘኛል፤ አምላኬ የጠላቶቼን ውድቀት ያሳየኛል።
11
ጋሻችን ጌታ ሆይ፤ አትግደላቸው፤ አለዚያ ሕዝቤ ይረሳል፤ በኀይልህ አንከራትታቸው፤ ዝቅ ዝቅም አድርጋቸው።
12
ከአፋቸው ስለሚወጣው ኀጢአት፣ ከከንፈራቸውም ስለሚሰነዘረው ቃል፣ በትዕቢታቸው ይያዙ። ስለ ተናገሩት መርገምና ውሸት፣
13
በቍጣ አጥፋቸው፤ ፈጽመህም አስወግዳቸው፤ በዚህም እግዚአብሔር የያዕቆብ ገዥ መሆኑ፣ እስከ ምድር ዳርቻ ይታወቃል።
14
እንደ ውሻ እያላዘኑ፣ በምሽት ተመልሰው ይመጣሉ፤ በከተማዪቱም ዙሪያ ይራወጣሉ።
15
ምግብ ፍለጋ ይራወጣሉ። ካልጠገቡም ያላዝናሉ።
16
እኔ ግን ስለ ኀይልህ እዘምራለሁ፤ በማለዳም ስለ ምሕረትህ እዘምራለሁ፤ አንተ መጠጊያዬ፣ በመከራም ቀን ዐምባዬ ነህና።
17
ብርታቴ ሆይ፤ ውዳሴ አቀርብልሃለሁ፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ መጠጊያዬ፣ የምትወድደኝም አምላኬ ነህና።
← Chapter 58
Chapter 60 →