bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Psalms 45
Psalms 45
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
ልቤ መልካም ሐሳብ አፈለቀ፤ የተቀኘሁትን ቅኔ ለንጉሥ አሰማለሁ፤ አንደበቴም እንደ ባለሙያ ጸሓፊ ብርዕ ነው።
2
አንተ ከሰዎች ሁሉ ይልቅ ውብ ነህ፤ ከንፈሮችህም የጸጋ ቃል ያፈልቃሉ፤ ስለዚህ እግዚአብሔር ለዘላለም ባርኮሃል።
3
ኀያል ሆይ፤ ሰይፍህን በወገብህ ታጠቅ፤ ግርማ ሞገስንም ተላበስ።
4
ስለ እውነት፣ ስለ ትሕትና፣ ስለ ጽድቅ ሞገስን ተጐናጽፈህ በድል አድራጊነት ገሥግሥ፤ ቀኝ እጅህም ድንቅ ተግባር ታሳይ።
5
የሾሉ ፍላጻዎችህ በንጉሥ ጠላቶች ልብ ይሰካሉ፤ ሕዝቦችም ከእግርህ በታች ይወድቃሉ።
6
አምላክ ሆይ፤ ዙፋንህ ከዘላለም እስከ ዘላለም ይኖራል፤ የመንግሥትህ በትር የቅንነት በትር ናት።
7
ጽድቅን ወደድህ፤ ዐመፃን ጠላህ፤ ስለዚህ እግዚአብሔር አምላክህ፣ ከጓደኞችህ ይልቅ አንተን የደስታ ዘይት ቀባህ።
8
ልብስህ ሁሉ በከርቤ፣ በአደስና በጥንጁት መዐዛ ያውዳል፤ በዝኆን ጥርስ ከተዋቡ ቤተ መንግሥቶችም፣ የበገናና የመሰንቆ ድምፅ ደስ ያሰኙሃል።
9
ከተከበሩት ሴቶችህ መካከል የነገሥታት ሴቶች ልጆች ይገኛሉ፤ ንግሥቲቱም በኦፊር ወርቅ አጊጣ በቀኝህ ቆማለች።
10
ልጄ ሆይ፤ አድምጪ፤ አስተውዪ፤ ጆሮሽንም አዘንብዪ፤ ሕዝብሽንና የአባትሽን ቤት እርሺ።
11
ንጉሥ በውበትሽ ተማርኳል፤ ጌታሽ ነውና አክብሪው።
12
የጢሮስ ሴት ልጅ እጅ መንሻ ይዛ ትመጣለች፤ ሀብታሞችም ደጅ ይጠኑሻል።
13
የንጉሥ ልጅ ከላይ እስከ ታች ተሸልማ እልፍኟ ውስጥ አለች፤ ልብሷም ወርቀ ዘቦ ነው።
14
በጥልፍ ሥራ ባጌጠ ልብስ ወደ ንጉሥ ትወሰዳለች፤ ደናግል ጓደኞቿም ተከትለዋት፣ ወደ አንተ ይመጣሉ።
15
በደስታና በሐሤት ወደ ውስጥ ይመሯቸዋል፤ ወደ ንጉሡም ቤተ መንግሥት ይገባሉ።
16
ወንዶች ልጆችህ በአባቶችህ እግር ይተካሉ፤ ገዦችም አድርገሽ በምድር ሁሉ ትሾሚያቸዋለሽ።
17
ስምሽን በትውልድ ሁሉ ዘንድ መታሰቢያ አደርጋለሁ፤ ስለዚህ ሕዝቦች ከዘላለም እስከ ዘላለም ያወድሱሃል።
← Chapter 44
Chapter 46 →