bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Psalms 44
Psalms 44
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
አምላክ ሆይ፤ በጆሯችን ሰምተናል፤ አባቶቻችን በቀድሞ ዘመን፣ እነርሱ በነበሩበት ዘመን፣ ያደረግኸውን ነግረውናል።
2
ሕዝቦችን በእጅህ አሳድደህ አወጣሃቸው፤ አባቶቻችንን ግን ተከልሃቸው፤ ሕዝቦችን አደቀቅህ፤ አባቶቻችንን ግን ነጻ አወጣሃቸው።
3
ምድሪቱን የወረሱት በሰይፋቸው አልነበረም፤ ድልንም የተጐናጸፉት በክንዳቸው አይደለም፤ አንተ ወድደሃቸዋልና ቀኝ እጅህ፣ ክንድህና የፊትህ ብርሃን ይህን አደረገ።
4
እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ንጉሤ ነህ፤ ያዕቆብም ድል እንዲያደርግ የወሰንህ አንተ ነህ።
5
በአንተ ጠላቶቻችን በመጡበት እንዲመለሱ እናደርጋለን፤ በስምህም ባላጋራዎቻችንን ከእግራችን በታች እንረግጣለን።
6
በቀስቴ አልተማመንም፤ ሰይፌም አያስጥለኝም።
7
አንተ ግን በጠላቶቻችን ላይ ድልን ትሰጠናለህ፤ ባላንጣዎቻችንንም ታሳፍራለህ።
8
ዘወትር በእግዚአብሔር እንመካለን፤ ስምህንም ለዘላለም እንወድሳለን።
9
አሁን ግን እነሆ ትተኸናል፤ አሳፍረኸናልም፤ ከሰራዊታችንም ጋር አትወጣም።
10
ከጠላት ፊት እንድናፈገፍግ አደረግኸን፤ ባላንጣዎቻችንም ዘረፉን።
11
እንደሚታረዱ በጎች አደረግኸን፤ በሕዝቦችም መካከል በተንኸን።
12
ሕዝብህን በርካሽ ዋጋ ሸጥኸው፤ ከሽያጩም ያገኘኸው ትርፍ የለም።
13
ለጎረቤቶቻችን ስድብ፣ በዙሪያችን ላሉትም መሣቂያና መዘበቻ አደረግኸን።
14
በሕዝቦች ዘንድ መተረቻ፣ በሰዎች መካከል በንቀት ራስ መነቅነቂያ አደረግኸን።
15
ውርደቴ ቀኑን ሙሉ በፊቴ ነው፤ ፊቴም ዕፍረትን ተከናንቧል።
16
ይህም ከሚዘልፍና ከሚያላግጥ ሰው ድምፅ የተነሣ፣ ከጠላትና ከተበቃይ ሁኔታ የተነሣ ነው።
17
አንተን ሳንረሳ፣ ለኪዳንህም ታማኝነታችንን ሳናጓድል፣ ይህ ሁሉ ደረሰብን።
18
ልባችን ወደ ኋላ አላለም፤ እግራችንም ከመንገድህ አልወጣም።
19
አንተ ግን ተኵላዎች በሚውሉበት ቦታ ሰባብረህ ጣልኸን፤ በሞት ጥላም ሸፈንኸን።
20
የአምላካችንን ስም ረስተን፣ እጃችንንም ወደ ባዕድ አምላክ ዘርግተን ቢሆን ኖሮ፣
21
እግዚአብሔር ይህን ማወቅ ይሳነዋልን? እርሱ ልብ የሰወረውን የሚረዳ ነውና።
22
ይሁን እንጂ ቀኑን ሙሉ ስለ አንተ ሞትን እንጋፈጣለን፤ እንደሚታረዱ በጎችም ተቈጥረናል።
23
ጌታ ሆይ፤ ንቃ! ለምንስ ትተኛለህ? ተነሥ፤ ለዘላለምም አትጣለን።
24
ፊትህን ለምን ትሰውራለህ? መከራችንንና መጠቃታችንን ለምን ትረሳለህ?
25
ነፍሳችን ዐፈር ውስጥ ሰጥማለች፤ ሆዳችንም ከምድር ጋር ተጣብቋል።
26
ተነሥና እርዳን! ስለ ምሕረትህ ስትል ተቤዠን።
← Chapter 43
Chapter 45 →