bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Psalms 39
Psalms 39
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
እኔ፣ “በአንደበቴ እንዳልበድል፣ መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ክፉዎችም በእኔ ዘንድ እስካሉ ድረስ፣ ልጓም በአፌ አስገባለሁ” አልሁ።
2
እንደ ዲዳ ዝም አልሁ፤ ለበጎ ነገር እንኳ አፌን ዘጋሁ፤ ሆኖም ጭንቀቴ ባሰ።
3
ልቤ በውስጤ ጋለ፤ በማሰላስልበትም ጊዜ እሳቱ ነደደ፤ ከዚያም በአንደበቴ እንዲህ ተናገርሁ፤
4
“ እግዚአብሔር ሆይ፤ የሕይወቴን ፍጻሜ፣ የዘመኔንም ቍጥር አስታውቀኝ፤ ዐላፊ ጠፊ መሆኑንም ልረዳ።
5
እነሆ፤ ዘመኔን በስንዝር ለክተህ አስቀመጥህ፤ ዕድሜዬም በፊትህ እንደ ኢምንት ነው፤ በርግጥ የሰው ሁሉ ሕይወት ተን ነው።
6
“ሰው የጥላ ውልብታ ነው፤ በከንቱም ይታወካል፤ ለማን እንደሚሆን ሳያውቅ ሀብት ንብረት ያከማቻል።
7
“ጌታ ሆይ፤ አሁንስ ወደ ማን ልመልከት? ተስፋዬ በአንተ ላይ ነው።
8
ከኀጢአቴ ሁሉ አድነኝ፤ የሰነፎች መሣለቂያ አታድርገኝ።
9
ይህን ያደረግህ አንተ ነህና፣ ዝም እላለሁ፤ አፌንም አልከፍትም።
10
ክንድህን አንሣልኝ፤ ከእጅህ ምት የተነሣ ደክሜአለሁ።
11
ሰዎችን ስለ ኀጢአታቸው ለመቅጣት ትገሥጻቸዋለህ፤ ሀብታቸውንም ብል እንደ በላው ታደርጋለህ፤ በርግጥ ሰው ሁሉ ተን ብቻ ነው።
12
“ እግዚአብሔር ሆይ፤ ጸሎቴን ስማ፤ ጩኸቴን አድምጥ፤ ልቅሶዬንም ቸል አትበል፤ በአንተ ፊት እኔ መጻተኛ ነኝና፤ እንደ አባቶቼም እንግዳ ነኝ።
13
ላለመመለስ ከመሰናበቴ በፊት፣ ዳግመኛ ደስ ይለኝ ዘንድ ዐይንህን ከላዬ አንሣ።”
← Chapter 38
Chapter 40 →