bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Psalms 38
Psalms 38
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
እግዚአብሔር ሆይ፤ በቍጣህ አትገሥጸኝ፤ በመዓትህም አትቅጣኝ።
2
ፍላጻዎችህ ወግተውኛልና፤ እጅህም ተጭናኛለች።
3
ከቍጣህ የተነሣ ሰውነቴ ጤና አጥቷል፤ ከኀጢአቴም የተነሣ ዐጥንቶቼ ሰላም የላቸውም።
4
በደሌ ውጦኛል፤ እንደ ከባድ ሸክምም ተጭኖኛል።
5
ከንዝህላልነቴ የተነሣ፣ ቍስሌ ሸተተ፤ መገለም፤
6
ዐንገቴን ደፋሁ፤ ጐበጥሁም፤ ቀኑንም ሙሉ በትካዜ ተመላለስሁ።
7
ወገቤ እንደ እሳት ነድዷል፤ ሰውነቴም ጤና የለውም።
8
እጅግ ዝያለሁ፤ ፈጽሞም ደቅቄአለሁ፤ ከልቤም መታወክ የተነሣ እጮኻለሁ።
9
ጌታ ሆይ፤ ምኞቴ ሁሉ በፊትህ ግልጽ ነው፤ ጭንቀቴም ከአንተ የተሰወረ አይደለም።
10
ልቤ በኀይል ይመታል፤ ጕልበት ከድቶኛል፤ የዐይኔም ብርሃን ጠፍቷል።
11
ከቍስሌ የተነሣ ወዳጆቼም ባልንጀሮቼም ሸሹኝ፤ ጎረቤቶቼም ርቀው ቆሙ።
12
ሕይወቴን ለማጥፋት የሚሹ ወጥመድ ዘረጉብኝ፤ ሊጐዱኝ የሚፈልጉ ሊያጠፉኝ ዛቱ፤ ቀኑንም ሙሉ ተንኰል ይሸርባሉ።
13
እኔ ግን እንደማይሰማ ደንቈሮ፣ አፉንም መክፈት እንደማይችል ዲዳ ሆንሁ።
14
በርግጥም ጆሮው እንደማይሰማ፣ አንደበቱም መልስ መስጠት እንደማይችል ሰው ሆንሁ።
15
እግዚአብሔር ሆይ፤ በተስፋ እጠብቅሃለሁ፤ ጌታ አምላኬ ሆይ፤ አንተ መልስ ትሰጠኛለህ።
16
እኔ፣ “ጠላቶቼ በእኔ ላይ ደስ አይበላቸው፤ እግሬም ሲንሸራተት፣ በላዬ አይኵራሩብኝ” ብያለሁና።
17
ልወድቅ ተቃርቤአለሁ፤ ከሥቃዬም ከቶ አልተላቀቅሁም።
18
በደሌን እናዘዛለሁ፤ ኀጢአቴም አውካኛለች።
19
ብርቱዎች ጠላቶቼ ብዙ ናቸው፤ ያለ ምክንያት የሚጠሉኝም ስፍር ቍጥር የላቸውም።
20
መልካሙን ስለ ተከተልሁ፣ በበጎ ፈንታ ክፉ የሚመልሱልኝ ጠሉኝ።
21
እግዚአብሔር ሆይ፤ አትተወኝ፤ አምላኬ ሆይ፤ ከእኔ አትራቅ።
22
ጌታዬ መድኅኔ ሆይ፤ እኔን ለመርዳት ፍጠን።
← Chapter 37
Chapter 39 →