bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Psalms 17
Psalms 17
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
እግዚአብሔር ሆይ፤ በቅንነት የቀረበውን አቤቱታዬን ስማ፤ ጩኸቴንም አድምጥ፤ ከአታላይ ከንፈር ያልወጣውን፣ ጸሎቴን አድምጥ።
2
ጽድቄ ከአንተ ዘንድ ይምጣ፤ ዐይኖችህም ፍትሕን ይዩ።
3
ልቤን መረመርኸው፣ በሌሊት ጠጋ ብለህ ፈተንኸኝ፤ ፈተሽኸኝ አንዳች አላገኘህብኝም፤ አንደበቴም ዕላፊ አልሄደም።
4
ከሰዎች ተግባር፣ በከንፈርህ ቃል፣ ከዐመፀኞች መንገድ፣ ራሴን ጠብቄአለሁ።
5
አረማመዴ በመንገድህ ጸንቷል እግሮቼም አልተንሸራተቱም።
6
አምላክ ሆይ፤ ስለምትመልስልኝ አንተን እጣራለሁ፤ ጆሮህን ወደ እኔ ጣል አድርገህ ጸሎቴን ስማ።
7
ከጠላቶቻቸው መተገኛ ያደረጉህን፣ በቀኝ እጅህ የምትታደግ ሆይ፤ ጽኑ ፍቅርህን ድንቅ አድርገህ ግለጥ።
8
እንደ ዐይንህ ብሌን ጠብቀኝ፤ በክንፎችህም ጥላ ሰውረኝ፤
9
ከሚያስጨንቁኝ ከክፉዎች፣ ከሚከብቡኝ አደገኛ ባላንጣዎቼ ጋርደኝ።
10
ደንዳና ልባቸውን ደፈኑት፤ በአፋቸውም ትዕቢት ይናገራሉ።
11
አሳድደው ደረሱብኝ፤ ከበቡኝም፤ መሬት ላይ ሊዘርሩኝም አፈጠጡብኝ።
12
እነርሱ ለንጥቂያ እንደሚጓጓ አንበሳ፣ በስውርም እንደሚያደባ ደቦል አንበሳ ናቸው።
13
እግዚአብሔር ሆይ፤ ተነሥተህ ግጠማቸውና ጣላቸው፤ በሰይፍህም ከክፉዎች ታደገኝ።
14
እግዚአብሔር ሆይ፤ እንዲህ ካሉት ሰዎች በክንድህ አድነኝ፤ ዕድል ፈንታቸው ይህችው ሕይወት ብቻ ከሆነች፣ ከዚህ ዓለም ሰዎች ታደገኝ። ከመዝገብህ ሆዳቸውን ሞላህ፤ ልጆቻቸውም ተትረፍርፎላቸዋል፤ ለልጆቻቸውም ሀብት ያከማቻሉ።
15
እኔ ግን በጽድቅ ፊትህን አያለሁ፤ ስነቃም ክብርህን አይቼ እረካለሁ።
← Chapter 16
Chapter 18 →