bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Psalms 16
Psalms 16
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
አምላክ ሆይ፤ መጠጊያዬ ነህና፣ በከለላህ ሰውረኝ።
2
እግዚአብሔርን ፣ “አንተ ጌታዬ ነህ፤ ከአንተ በቀር በጎነት የለኝም” አልሁት።
3
በምድር ያሉ ቅዱሳን፣ ሙሉ ደስታ የማገኝባቸው ክቡራን ናቸው።
4
ሌሎችን አማልክት የሚከተሉ፣ ሐዘናቸው ይበዛል፤ እኔ ግን የደም ቍርባናቸውን አላፈስስም፤ ስማቸውንም በአፌ አልጠራም፤
5
እግዚአብሔር የርስት ድርሻዬና ጽዋዬ ነው፤ ዕጣዬም በእጅህ ናት።
6
መካለያ ገመድ ባማረ ስፍራ ተጥሎልኛል፤ በርግጥም የተዋበች ርስት አግኝቻለሁ።
7
የሚመክረኝን እግዚአብሔርን እባርካለሁ፤ በሌሊት እንኳ ልቤ ቀናውን ያመላክተኛል።
8
እግዚአብሔርን ሁልጊዜ በፊቴ አድርጌአለሁ፤ እርሱ በቀኜ ስላለ አልናወጥም።
9
ስለዚህ ልቤ ደስ አለው፤ ነፍሴም ሐሤት አደረገች፤ ሥጋዬም ያለ ሥጋት ዐርፎ ይቀመጣል፤
10
በሲኦል ውስጥ አትተወኝምና፤ ቅዱስህም መበስበስን እንዲያይ አታደርግም።
11
የሕይወትን መንገድ ታሳየኛለህ፤ በአንተ ዘንድ የደስታ ሙላት፣ በቀኝህም የዘላለም ፍሥሓ አለ።
← Chapter 15
Chapter 17 →