bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Psalms 147
Psalms 147
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
ሃሌ ሉያ። አምላካችንን በመዝሙር ማወደስ እንዴት መልካም ነው! እርሱን ማመስገን ደስ ያሰኛል፤ ይህ ተገቢም ነው።
2
እግዚአብሔር ኢየሩሳሌምን መልሶ ይሠራታል፤ ከእስራኤል የተበተኑትን ይሰበስባል።
3
ልባቸው የተሰበረውን ይፈውሳል፤ ቍስላቸውንም ይጠግናል።
4
የከዋክብትን ብዛት ያውቃል፤ እያንዳንዱንም በስሙ ይጠራዋል።
5
ጌታችን ታላቅ ነው፤ እጅግ ኀያልም ነው፤ ለጥበቡም ወሰን የለውም።
6
እግዚአብሔር ትሑታንን ከፍ ያደርጋል፤ ክፉዎችን ግን ወደ ምድር ይጥላል።
7
ለእግዚአብሔር በምስጋና ዘምሩ፤ ለአምላካችንም በመሰንቆ ምስጋና አቅርቡ።
8
ሰማይን በደመናት የሚሸፍን እርሱ ነው፤ ለምድርም ዝናብን ይሰጣል፤ በተራሮችም ላይ ሣር ያበቅላል።
9
ለእንስሳት ምግባቸውን፣ የቍራ ጫጩቶችም ሲንጫጩ የሚበሉትን ይሰጣቸዋል።
10
እርሱ በፈረስ ኀይል አይደሰትም፤ በሯጭም ብርታት ላይ ደስታውን አያደርግም።
11
ነገር ግን እግዚአብሔር በሚፈሩት፣ በምሕረቱ በሚታመኑትም ይደሰታል።
12
ኢየሩሳሌም ሆይ፤ እግዚአብሔርን አመስግኚ፤ ጽዮን ሆይ፤ አምላክሽን አወድሺ፤
13
እርሱ የደጆችሽን መወርወሪያ አጽንቷልና፤ ልጆችሽንም በውስጥሽ ባርኳል።
14
በድንበርሽ ውስጥ ሰላም ያሰፍናል፤ ማለፊያ ስንዴም ያጠግብሻል።
15
ትእዛዙን ወደ ምድር ይልካል፤ ቃሉም እጅግ በፍጥነት ይሮጣል።
16
ዐመዳዩን እንደ በርኖስ ይዘረጋል፤ ውርጩን እንደ ዐመድ ይነሰንሳል።
17
የበረዶውን ድንጋይ ቍልቍል ይወረውረዋል፤ በውሽንፍሩስ ቅዝቃዜ ፊት ማን ሊቆም ይችላል?
18
ቃሉን ልኮ ያቀልጣቸዋል፤ ነፋሱን ያነፍሳል፤ ውሆችንም ያፈስሳል።
19
ቃሉን ለያዕቆብ፣ ሥርዐቱንና ፍርዱን ለእስራኤል ይገልጣል።
20
ይህን ለማንኛውም ሌላ ሕዝብ አላደረገም፤ እነርሱም ፍርዱን አላወቁም። ሃሌ ሉያ።
← Chapter 146
Chapter 148 →